ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩ 23 የደርግ መንግሥት ባለስልጣናት ቅጣታቸው በዕድሜ ልክ እሥራት መሻሻሉን ፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ይፋ አደረጉ።
ህንድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት አፍሪካ የልማት ግቦችዋን ታሳካ ዘንድ ለመርዳት አምስት ቢሊዮን ዶላር በብድር ለመስጠት ቃል ገባች ። ኢትዮጲያንና ጅቡቲን የሚያገናኝ አዲስ የባቡር መስመር ለመዘርጋትም ሶስት መቶ ሚሊዮን ዶላር አበድራለሁ ብላለች።
ባለፈው ሣምንት ይፋ የተደረገው የዲቪ ዕድለኞች ዝርዝር መሠረዙን የአሜሪካ ኤምባሲ ኮንሱላር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡
ቀደም ባሉት ዓመታት ወባ በሽታ በአብዛኞቹ የኢትዮጲያ ክፍሎች ገዳይ በሽታ እንደነበር ይታወቃል ። ዛሬ ግን ይህ ገጽታ መለወጡን የጤና ባለሙያዎች ይመሰክራሉ።
በአዲስ አበባ በስፋት የሚካሄዱ የግንባታ ስራዎች በርካታ ቤተሰቦችን ወደሌላ አካባቢ እያዛወሩ ነው።
ምርጫ 2002ን ለማወከ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የተባሉ ሰዎች እስከ 20 አመት በሚደርስ እስራት በፍርድ ቤት ተቀጥተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ይፋ ያደረገውን ፖሊሲ በደስታ እንደተቀበሉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኰሚሽነር ተወካይ ገለፁ።
ከ3.4 ሚሊዮን አመታት በፊት የሰው ልጅ ከድንጋይ የተሰሩ ቁሳቁሶችን በኢትዮጵያ ይጠቀም እንደነበረ አንድ ባለሙያ አስታወቁ።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በደራሲያን ምስል የታተሙ ቴምብሮች ለስርጭት በቅተዋል።
ምርጫው ከፍተኛ ብዛት ያላቸው መራጮች የተሳተፉበትና ሰላማዊ ቢሆንም እየጠበበ በሄደው የፖለቲካ ምህዳርና እኩልነት በጎደለው የመወዳደርያ ሜዳ መዘፈቁ አልቀርም ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ገለጹ።
በፊታችን እሁድ ብሔራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ታዛቢዎቻችንን ያስፈራራል፣ አልያም በገንዘብ ይደልላል አሉ። ከመንግስት ወይም ከምርጫ ቦርድ ምላሽ አልተገኘም።
የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን መድረክ ታዛበዎቹ በምርጫ ዉጤት ላይ እንዳይፈርሙ ማሳመን ጀምሮአል፣በአገሪቱ ዴሞክራሲ የራሱን አስተዋጽኦ አያደርግም ሲሉ ከሰዋል።
ድርጅቱ ከምርጫ እራሱን ያገለለው የኢህአዴግ አባል ድርጅት ታዛቢዎቼ ለምርጫ እንዳይመዘገቡና የምርጫ ካርድ እንዳያገኙ በማድርግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያጸደቁትን የምርጫ ህግ ጥሷል ሲል ነው።