በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ መፈቀዱ UNHCRን አስደሰተ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ መፈቀዱ UNHCRን አስደሰተ


በኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኰሚሽነር ተጠሪ ሚስተር ሞሰስ ኦኬሎ በተለይ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግልጽ እንዳደረጉት የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በብዙ መንገድ አንድ ናቸው ብለዋል።

ኤርትራ በሬፈረንደም እራሷን የቻለች ነፃ ሀገር ከሆነች ወዲህ፥ በዚያች ሀገር በተፈጠሩ ምክንያቶች ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መሰደድ ጀምረዋል። በሚስተር ኦኬሎ ቃል መሠረት ቀደም ሲል የነዚህ ስደተኞች ቁጥር፥ ወደ 60ሺህ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፤ ከዚህ ወደ ሌላ ሦስተኛ ሀገር በመሄዳቸው ዛሬ ቁጥራቸው ወደ ሰላሳ ስድስት ሺህ ወርዷል።

ሚስተር ኦኬሎ እንዳብራሩት ስደተኞቹ እነዚህን ካምፖች ለቀው ለመውጣት አንዳንድ መሠረታዊ ናቸው የተባሉ ጉዳዮችን ማሟላት አለባቸው ብለዋል።

ሲያብራሩም የመጀመሪያው መሟላት ያለበት ነጥብ ማንም ኤርትራዊ ስደተኛ ሊደግፈው የሚችለው ዘመድ እስካለው ድረስ፣ ወይም እነዚህ ከካምፕ ሊወጡ የሚፈልጉ ኤርትራውያን ከካምፕ ውጭ እራሳቸውን የሚችሉበት መንገድ እንዳላቸው እስካረጋገጡ ድረስ ይህንን ለማድረግ ይፈቀድላቸዋል።

ይህም ለኤርትራውያን በጣም ለቀቅ ያለና የሚያዝናና ፖሊሲ ነው። ምክንያቱም አንዳንዶቹ እንዲያውም ብዙዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመዶች አሏቸው። ብዙዎቹም ከካምፑ ውጭ እራሳቸውን ለማኖር የሚያስችላቸው መንገድ አላቸው። ስለሆነም ይህን ፖሊሲ እኛም ሆን አያሌ ኤርትራውያን ስደተኞች በደስታ ተቀብለነዋል ሲሉ በሰፊው አብራርተዋል።

መሥራት ይፈቀድላቸው እንደሁ ተጠይቀው ሲመልሱም፥

ሥራ እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም። ከካምፕ ወጥቶ በገበያ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ጋር ለሥራ መወዳደር አይችሉም። እነዚህ ስደተኞች እዚህ የመጡት መጠጊያ ፈልገው መሆኑን ከለላ ለማግኘት የመጡና ወደፊትም ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ተስፋ የሚያደርጉ ወንድሞቻቸው መሆናቸውን ለኢትዮጵያውያን አረጋግጣለሁ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG