በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የቅድመ-ሰው መገኛና የቴክኖሎጂ መጀመሪያ መሆኗን የሚጠቁም ግኝት ይፋ ሆነ


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚዚየም በኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ዶክተር ዘረሰናይ አለምሰገድ ይፋ የሆነው የጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው፤ ቅድመ-ሰው ከ3.4 ሚሊዮን አመታት በፊት ከድንጋይ የተሰሩ ቁሶችን ይገለገል ነበር።

“ዛሬ ከፊት ለፊታችሁ የምገኘው በአለም ላይ የሰው ልጅ ቴክኖሎጂን ተጠቅሟል በሚል የተቀመጠውን ሳይንሳዊ መላምት በአንድ ሚሊዮን አመት ወደኋላ የሚገፋ ግኝት ይዤ ነው” ብለዋል ዶክተር ዘረሰናይ።

በዚህ ጥናት የሰው ልጅ ከድንጋይ የሰራቸውን ቁሳቁሶች ተጠቅሞ የትላልቅ አጥቢ እንስሳትን ለማደን፣ ስጋቸውን ለመብላትና መቅኒያቸውን ለመምጠጥ አቅሙ እንደነበረው ተጠቁሟል።

በካሊፎርኒያ የሳይንስ አካዳሚ የአንትሮፖሎጂ ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ዘረሰናይ “ኢትዮጵያ የቅድመ-ሰው ዘር መገኛ ብቻ ሳትሆን፤ የመጀመሪያው ቴክኖሎጂ መገኛ እንደሆነች የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG