በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንድ እና የአፍሪካ ሁለተኛ የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ

ህንድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት አፍሪካ የልማት ግቦችዋን ታሳካ ዘንድ ለመርዳት አምስት ቢሊዮን ዶላር በብድር ለመስጠት ቃል ገባች ። ኢትዮጲያንና ጅቡቲን የሚያገናኝ አዲስ የባቡር መስመር ለመዘርጋትም ሶስት መቶ ሚሊዮን ዶላር አበድራለሁ ብላለች።

ህንድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት አፍሪካ የልማት ግቦችዋን ታሳካ ዘንድ ለመርዳት አምስት ቢሊዮን ዶላር በብድር ለመስጠት ቃል ገባች ። ኢትዮጲያንና ጅቡቲን የሚያገናኝ አዲስ የባቡር መስመር ለመዘርጋትም ሶስት መቶ ሚሊዮን ዶላር አበድራለሁ ብላለች።

ይህን የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሞሐን ሲንግ ይፋ ያደረጉት ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ የህንድ እና የአፍሪካ ሁለተኛ የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ላይ ነው።

ይህ ሁለተኛው የህንድ እና አፍሪካ መድረክ የመጀመሪያውን ጉባዔ ያደረገው እኤአ በሁለት ሺህ ስምንት ዓመተ ምህረት በህንድ ዋና ከተማ በኒው ዴልሂ እንደነበር ይታወሳል።

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው በሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመት አፍሪካ ከዓለም ዋነኛ የዕድገት ዋልታዎች አንዷ እንደምትሆን ገልጠው ይህን ዕምቅ ችሎታ ተጨባጭ ለማድረግ ህንድ ከአፍሪካ ጋር ለመስራት መዘጋጀቷን አስገንዝበዋል።

ዘገባውን ያድምጡ

XS
SM
MD
LG