በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ሰላማዊ ቢሆንም በእኩል ሜዳ አለመደረጉን ገለጸ


ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 አም በኢትዮጵያ የተካሂደውን ምክር ቤታዊ ምርጫ የተከታተለው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን የምርጫውን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎን ሲገመግሙ አራተኛው አጠቃላይ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ባለድርሻ አካላት በአንድነት ተቀብለውታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድም ምርጫውን በበቂ ሁኔታ አስተዳድሯል። ይሁንና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚነሱትን የኢወገኝተኛነት ጥያቄን ለመመለስ አልቻለም ብለዋል በርማን።

ታይስ በርማን ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከእኩለ ቀን በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ሚስተር በርማን በተጨማሪም “በገዢው ፓርቲና በመንግስታዊ አስተዳደር መካከል መኖር የሚገባው ልዩነት በብዙ የተለያዩ ቦታዎች ደብዝዞ ታይቷል። የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመንግስት ንብረቶች ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ መገልገያነት መዋላቸውን አስተውሏል። ቡድኑ የ 2002 የምርጫ ሜዳ በበቂ ሚዛን አልጠበቀም። በብዙ ቦታዎች ለገዢው ፓርቲ ያጋደለ ነበር የሚል እምነት አለው።” በማለት ገምግመዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ቴክኒካዊ ችግሮችን ብቃት ባለው ሙያዊ ተግባር ተወጥቷል።

በማለትም አመስግነዋል። ሙሉ የምርጫ ጣብያዎች ዝርዝርን የመሳሰሉት መረጃዎች አለመኖራቸው ግን በሂደቱ ግልጽነት ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል።

ስለሚድያ ሲናገሩ ደግሞ የአሜሪካ ድምጽ ሪድዮ የአማርኛ አገልግሎት መታፈንም የመራጮችን ከዘርፈ ብዙ ምንጮች ኢንፎርመሻን የማግኘት ዕድል ቀንሷል ብለዋል የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን።

XS
SM
MD
LG