በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወባ በሽታ በድሬደዋ ታሪክ ሊሆን እየተቃረበ መሆኑ ተገለጠ።


ቀደም ባሉት ዓመታት ወባ በሽታ በአብዛኞቹ የኢትዮጲያ ክፍሎች ገዳይ በሽታ እንደነበር ይታወቃል ። ዛሬ ግን ይህ ገጽታ መለወጡን የጤና ባለሙያዎች ይመሰክራሉ።

ድሬደዋ ከተማና አካባቢዋ ቆላማ በመሆኑ የወባ ተጠቂ አካባቢ በሚባሉት ውስጥ ይመደባል። ከጥቂት ዓመታት በፊትም ወባ ዓመቱን በሙሉ የብዙ ሰዎችን ህይወት ይቀጥፍ ብዙዎችንም ለከባድ ህመምና ለአካል ጉዳት ይዳርግ ነበር ።

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ክልል ግን ወባ ታሪክ ሊሆን የተቃረበ ይመስላል። እንዴት ሊሆን ቻለ ?

የቪኦኤ ዘጋቢ መለስካቸው አምሃ ወደከተማይቱ ተጉዞ በነበረበት ባለፈው ሰሞን የድሬደዋ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌን ጠይቋል ።

ዶክተር ጽጌረዳ ሲያስረዱ በምዕተ ዓመቱ ግብ በተቀመጠው መሠረትና ባለፈው በሁለት ሺህ ሁለት ዓመተ ምህረት በተጠናቀቀው የአምስቱ ዓመት የጤና ዘርፍ ዕቅድ ላይ ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በስፋት ትኩረት ተደርጎ እንደነበር አውስተው በዚያም መሠረት በድሬደዋ ብርቱ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን አስገንዝበዋል።

ከዚያም በተጨማሪ የጤና ቢሮው በታቀደና በተቀናጀ ብርቱ ስራ በሽታውን ለማጥፋት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ዕምነት ይዞ መንቀሳቀሱንም አክለዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG