በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫን ለማወክና ሽብር ለመፍጠር አሲረዋል የተባሉ በእስራት ተቀጡ


ሰላሳ ሁለት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ተያዙ የተባሉት ሰዎች ከ13-19 ዓመት ተፈርዶባቸዋል

በትናንትናው ዕለት የታተመው አዲስ ዘመን፤የሀገሪቱን የፍትህ ሚንስቴር በመጥቀስ እንዳተተው፣ በእነዚህ ሽብር በመፍጠር እና ምርጫ 2002ን ለማደናቀፍ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ተያዙ ባላቸው ላይ፤ ፍርድ ቤት እስከ 20 አመት ፅኑ እስራት የሚደርስ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡

ጋዜጣው ጨምሮ እንዳብራራው፤ 32 ተከሳሾች በሐገር ውስጥ ሽብር በመፍጠር እና የ2 ሺህ ሁለትን ሐገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ ተልኮ ይዘው በሱዳን በኩል ሲገቡ፤ በጉዞ ላይ እንዳሉ ግንቦት 9 ቀን 2002 ዓ ም መያዛቸውን የፍትህ ሚንስቴር መግለጫ በመጥቀስ ያረጋግጣል፡፡

በተከሳሾቹ ላይ ከ13 እስከ 19 አመት የሚደርስ ቅጣት እንደተላለፈባቸው፤ ጋዜጣው አመልክቶ አቃቢ ህግ ያቀረበው ክስ፤ በሞት እና በእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም፤ ተከሳሾች ጥፋታቸውን በዝርዝር በማመናቸው፤ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ዝቅ አድርጎት ተከሳሾችን ያስተምራል፤ሌሎችንም ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይፈፅሙ ያስጠነቅቃል ያለውን ውሳኔ እንደሰጠ ጋዜጣው ገልፃል፡፡

ከ 1ኛ እስከ 5ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች በ19 አመት ፅኑ እስራት ሲቀጣ ከ18 አመት በታች ናቸው ያላቸውን 4 ተከሳሾች ግን እድሜያቸውን ከግምት በማስገባት ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸውን በ13 አመት ፅኑ እስራት ቀጥቷቸዋል ብሏል ጋዜጣው፡፡ በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 20 ቀን 2002 ዓ ም በዋለው ችሎት፤ 1ኛ ተከሳሽ 10 አለቃ ውቤ፣ጌትነት በ20 አመት፡፡ 2ኛ ተከሳሽ ምክትል የ10 አለቃ ታምራት አራጌ ደግሞ በ18 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ገልፃል፡፡

ተከሳሾቹ የተፈረደባቸው ወደ ኤርትራ በመሄድ ተልኮ በመቀበል እና ሐገር ውስጥ በመግባት የተሰጣቸውን ሽብር የመፍጠር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እያሉ መያዛቸውን ባቃቢ ህግ ማስረጃ በመረጋገጡ እንደሆነ፣ መግለጫውን በመግለፅ አዲስ ዘመን ያስረዳል፡፡

ከተከሳሾቹ በስተ ጀርባ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸውም ሆነ አለመኖራቸው ያልተገለፀ ቢሆንም አንዳንድ ታላላቅ የኢትዮጵያ መንግስት ባለ ስልጣናት ህገ-ወጥ ያሏቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች የኤርትራ መንግስት እንደተላላኪ በመጠቀም በኢትዮጵያ ሽብር ለመፍጠር እና ምርጫ 2 ሺህ ሁለትን ለማደናቀፍ እንደሚሞክር ሲከሱ መቆታቸው ይታወሳል፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG