በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዛቢዎቻች ማስፈራራት ይደርስባቸዉል አልያም በገንዘብ ይደለላሉ ሲሉ አማረሩ


የድምጽ መስጠቱ እሁድ ከጠዋቱ 12 ሰአት ላይ ይጀመራል

በምርጫዉ ዝግጅት ማብቂያ ላይ መጠናቀቅ ካለባቸዉ ጉዳዮች አንዱ እያንዳንዱ ተቃዋሚ ፓርቲ ለታዛቢነት የሚያቀርባቸዉን የስም ዝርዝር እስከ ሃሙስ ለምርጫ አስፈጻሚዉ አካል ማሳወቅ ነዉ። ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያዉያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ አቶ ልደቱ አያሌዉ ሲናገሩ፣ ድርጅታቸዉ 25 ሺህ ታዛቢዎች እንደሚያስፈልገዉና እያንዳንዱ እጩ በሚወዳደርበት የምርጫ ወረዳ ታዛቢዎችን መልምሎ እንዲያቀርብ መወሰኑን ገልጸዋል።

የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳም ለመድረክ እጩዎች የሚታዘቡ ሰዎች ስም ዝርዝር ከአስር ቀን በፊት በመላ ሃገሪቱ የምርጫ ጽህፈት ቤቶች ማቅረባቸዉን ገልጸዋል። የታዛቢዎች ስም ዝርዝር ከአስር ቀን በፊት እንዲቀርቡ መደረጉ ግን ታዛቢዎችን ለማስፈራራትና በገንዘብ ለመደለል አጋልጦአል ብለዋል።

(የሬድዮ ዘገባውን በገጹ በስተቀኝ ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG