በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የኦፌኮ ፓርቲ ታሳሪዎች አምስቱ በቀጠሮ ቀን ሳይቀርቡ ቀረ


አቶ በቀለ ገርባ
አቶ በቀለ ገርባ

አቃቢ ሕግ እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ከከሰሣቸው ሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች መካከል አምስቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ፍርድ ቤት ተገደው የመጡና ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውም ተናገሩ፤ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ተሟልተው እንዲቀርቡ ትዛዝ ሰጥቶ ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

ነሐሴ 5ቀን 2008 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስራ ዘጠነኛው ወንጀል ችሎት በሠጠው ብይንና ቀጠሮ መሠረት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግርስ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ ጎርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡት የአቃቢ ሕግን ምስክሮችን ለመስማት ነበረ፡፡

መለስካቸው አምሃ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የኦፌኮ ፓርቲ ታሳሪዎች አምስቱ በቀጠሮ ቀን ሳይቀርቡ ቀረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00

XS
SM
MD
LG