በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ ተከስቷል


ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ

በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ በስድሣ ቀበሌዎች ውስጥ አስቸኳይ የውኃ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

እርዳታ ምግብ ተቀባይነት በአንደኛ ደረጃ በተያዙ ወረዳዎች ያለው የምግብ ሥርጭት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል ተብሏል፡፡

በሚቀጥሉት ወራት የተረጂዎች ቁጥር በግማሽ ያህል ሊቀንስ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

በተያያዘ ዜና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ የኢትዮጵያ ፅሕፈት ቤት ከአራት ቀናት በፊት ኅዳር 12 በኢትዮጵያ ስላለው የድርቅ ሁኔታ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ቁልፍ ጉዳዮች ብሎ በዚህ መግለጫው የጠቀሰው በኢትዮጵያ በኤልኒኞ ምክንያት የተባባሰው ድርቅ በበርካታ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ እንዲሁም የበሽታዎች መከሰት ከመሠረታዊ የሕዝብ አግልግሎቶች መቋረጥ ጋር ተዳምሮ አሥር ሚሊዮን የሚጠጋ ኢትዮጵያውያን ሕይወት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ብሏል፡፡

በእነዚህ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሠቱ ችግሮች እስከያዝነው የአውሮፓ ዓመት ፍፃሜ አስቸኳይ እርዳታ ለማግኘት የተደረገው ጥረት እንዳልተሳካ የመንግሥታቱ ድርጅት የሠብዓዊ ጉዳዮች መርኃግብር ይጠቅስና ከእነዚህ አስቸኳይ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና የተባሉ ችግሮች መካከል የምግብ እጥረት፣ የተቀማጥ ችግርና የከብቶች ጤና አግልግሎት ተጠቅሰዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በምሥራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ ተከስቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:42 0:00

XS
SM
MD
LG