በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር መረራ ጉዲና ማዕከላዊ እንደሚገኙ ኦፌኮ ገለፀ


ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሰሩት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት ማድረግን በሚከለክለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

በአውሮፓ ህብረት የምስክር ሸንጎ ሠሚ ችሎት ፊት ቀርበው የተናገሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሠባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጎን ተቀምጠው የሚያሳዩ ምስሎች በድረገፅ ሲሰራጭ ቆይቷል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰራቸውን ቤተሰባቸው፣ ፓርቲያቸውና በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተቋቋመው ወታደራዊ እዝ ገልጿል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አቶ ጥሩነህ ገምታ ዛሬ ለቪኦኤ እንዳብራሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና በፓርቲ ተልዕኮ ሥራቸውን ለአንድ ወር ያህል ሲያከናውኑ ቆይተው፣ ትናንት ኅዳር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ቤታቸውም እስከ ምሽቱ 2፡00 ሠዓት ድረስ በረፍት ላይ እንደነበሩ አቶ ጥሩነህ ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና ማዕከላዊ እንደሚገኙ የኦፌኮ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

XS
SM
MD
LG