በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ለፊደል ካስትሮ የስንብት ሥነ ሥርዓት አካሄዱ


ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ
ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ

“በአህጉራችን ስለፊደል ካስትሮ ያለው ስሜት ተመሣሣይ ነው” ብለዋል የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስቱስ ሙኤንቻ፡፡ ምክትል ሊቀመንበሩ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል “ከእርሳቸው የተሻለ ወዳጅ ሊኖረን አይችልም” ብለዋል፡፡

ስሜት የተቀላቀለበት የሀዘን ድባብ ያጠላበት የፊደል ካስሮ መታሠቢያ ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ በ1970ዎቹ በኩባ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ባዘጋጁትና በብዛት በተገኙበት በዚህ ሥነ ሥርዓት ሌሎች እንግዶችም ታድመዋል፡፡

ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን ለፊደል ካስትሮ በአዲስ አበባ የስንብት ሥነ-ሥርዓት በማካሄድ ላይ
ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን ለፊደል ካስትሮ በአዲስ አበባ የስንብት ሥነ-ሥርዓት በማካሄድ ላይ

​ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆነ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የኅብረተሠብ ክፍሎች በስፍራው ነበሩ፡፡

የአፍሪካ ኅብረትን በመወከል የተገኙት የኅብረቱ ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሙኤንቻ ደግሞ ሀዘን ከፊታቸው እንባ፣ ከአይናቸው ይታይ ነበር፡፡

ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጁት የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ ሚስተር ኢራስቱስ ሙኤንቻን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኩባ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ለፊደል ካስትሮ የስንብት ሥነ ሥርዓት አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00

XS
SM
MD
LG