አዲስ አበባ —
የተለያዩ ዕቃዎችን እና ቁሳቁስ ገዝቶ ወደ ሃገር በማስገባት ብቻ ሀገርን ማሳደግ፣ ብሎም ማበለፀግ አይቻልም ሲሉ የኢትዮጵያው የሣይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስገነዘቡ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለተመረጡ የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ሽግግር ፍኖተ - ካርታ እንደተዘጋጀም ይፋ ተደርጓል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የቴክኖሎጂ መድረክም ተመሠረተ፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ትናንት አዘጋጅቶት በነበረ የአንድ ቀን አውደ ጥናት ላይ ከቀረቡት የጥናት ፁሑፎች መካከል የአውደ ጥናቱ ተካፋይ በነበረው የሣይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀ የቴክኖሎጂ ሽግግር ፍኖተ - ካርታ አንዱ ነበረ፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት በሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሚኒስትሩ የሣይንስ አማካሪ አቶ አብዱልራዛቅ ኡመር ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመታት በላይ ላስቆጠረ ረዥም ጊዜ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ ብትሆንም እስከዛሬ ድረስ ባለቤት እንዳልሆነችም ጠቁመዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ