በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ከሰኔ 2008 ዓ.ም. እስከ መስከረም መጨረሻ 2009 ዓ.ም. በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ «የስድሥት መቶ ስድሣ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል» ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከሰኔ 2008 ዓ.ም. እስከ መስከረም መጨረሻ 2009 ዓ.ም. በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ «የስድሥት መቶ ስድሣ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል» ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለፓርላማ ዛሬ ባቀረበው ሪፖርት ላይ በሌሎች አንድ ሺሕ አሥራ ስምንት ሰዎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች የደረሱበባቸው መሆኑንና በብዙ ሺኾች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አመልክቷል፡፡

Ethiopia Stampede
Ethiopia Stampede

ኮሚሽኑ አክሎም «የተፈጠረውን ሁከት ለመግታት የፀጥታ ኃይሎች በአንዳንድ ሥፍራ ሕጋዊና ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅመዋል፤ በሌሎች ደግሞ ተቃራኒው ተፈፅሟል» ብሏል፡፡

በመንግሥቱ የተቋቋመውና በመንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሰው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዚሁ ሪፖርቱ «የሁከቱ መንስዔ በአብዛኛው የመልካም አስተዳደር እጦትን እና ምጣኔ ኃብታዊ ችግር መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በዛሬው ሪፖርቱ ገልፆ እነዚህን መንስዔዎች ሕጋዊና ሕገወጥ የፖለቲካ ኃይሎች አባብሰዋቸዋል» ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው በዚህ ሪፖርቱ በአባባሽነትና በ”ዐመፅ ጠሪ”ነት የጠቀሳቸው የፖለቲካ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት መሪዎችበሰጡት አስተያየት ፤ ኮሚሽኑ የገለልተኝነት ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ ሪፖርቱ ተአማኒነት የለውም ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG