አዲስ አበባ —
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ የመጨረሻ የመከላከያ ማስረጃውን ለፍርድ ቤት አቀረበ፡፡ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን ተቀብሎ እንደሚመረምራቸው ገልፆ የፍርድ ውሳኔውን ለማሰማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት አቃቤ ሕግ የሽብር ወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል በሚል በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተበት የቀደሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ እንዲከላከል ከተወሰነበት በኋላ የመከላከያ ምስክሮቹን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ