በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀዲስ ዓለማየሁ የናስ ኃውልት ቆመላቸው


ለክብር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (1902 ዓ.ም. -1996 ዓ.ም.) መታሰቢያ የቆመ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት፤ ቅዳምን ገበያ - ደብረ ማርቆስ፤ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28/2009 ዓ.ም.
ለክብር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (1902 ዓ.ም. -1996 ዓ.ም.) መታሰቢያ የቆመ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት፤ ቅዳምን ገበያ - ደብረ ማርቆስ፤ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28/2009 ዓ.ም.

ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት ቆመላቸው፡፡

ጥቅምት 5/1902 ዓ.ም. ተወልደው ኅዳር 26/1996 ዓ.ም. ላረፉት ለሀዲስ ዓለማየሁ ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ የቆመውን ከነኀስ የተቀረፀ ኃውልት መርቀው የገለጡት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ወልደማርያም ናቸው፡፡

ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም፤ የኢትዮጵያ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ለሀዲስ ዓለማየሁ የቆመውን ኃውልት ሲመርቁ
ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም፤ የኢትዮጵያ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ለሀዲስ ዓለማየሁ የቆመውን ኃውልት ሲመርቁ

ደብረ ማርቆስ ከተማ ቅዳምን ገበያ ላይ ዛሬ በተከናወነው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ባሠራው የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ኃውልት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ቁጥሩ የበዛ የከተማዪቱ ነዋሪና ከሌሎችም አካባቢዎች የተሰባሰበ ሰው ተገኝቷል፡፡

የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ በሕይወት ሳሉ ያላሣተሟቸው ግጥሞቻቸውን የያዘ በዶ/ር ታየ አሰፋ የተዘጋጀና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሀዲስ ዓለማየሁ ጥናት ተቋም ዓመታዊ ጉባዔ ታትሞ እንዲወጣ የተደረገ መፅሐፍም ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡

ለክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ያዘጋጀው የፖስታ ቴምብር በኢትዮጵያ የፖስታ ድርጅት በ2002 ዓ.ም. ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡

«የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ፣ ተረት ተረት የመሠረት፣ ፍቅር እስከ መቃብር፣ ወንጀለኛ ዳኛ፣ የልም ዣት፣ ትዝታ» የሀዲስ ዓለማየሁ አዕምሮ ውልዶች ናቸው፡፡

ለተጨማሪ ከቅዳምን ገበያ፣ ደብረማርቆስ የተጠናቀረውን የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ሀዲስ ዓለማየሁ የናስ ኃውልት ቆመላቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG