በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጉድለቶች አሉበት ተባለ


ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሽግግር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ጉድለቶች እንዳሉት ጠ/ሚ ኃይለማሪያን ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሽግግር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ጉድለቶች እንዳሉት ጠ/ሚ ኃይለማሪያን ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ ምጣኔ ኃብታዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን በመጠበቅ ረገድ ሀገሪቱ የሚመሰገን ውጤት እንዳስመዘገበች ደግሞ አንዲት የዓለም አቀፋዊ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይተናገሩ፡፡

ትናንት አዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል በተከፈተው የሁለተኛው ብሔራዊ ሰብዓዊ መብቶች መርኃ ግብር የትግበራ ሥርዓት ማብሰሪያና የምክክር መድረክ ላይ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር ሠነዱ የተዘጋጀበትን ምክንያት በአፅንኦት አስመዝግበዋል፡፡

በእርሳቸው አባባል መንግሥት ሠነዱን ያዘጋጀው እንዲሁ የተለመደ አሠራር ስለሆነ አይደለም ወይንም ደግሞ የለጋሽ ድርጅቶችን ቀልብ ለማባበልም ተብሎ አይደለም፡፡ ሠነዱ የተዘጋጀው የሰብዓዊና የሀገሪቱ ሕልውና መሠረት መሆናቸውን በአግባቡ በመገንዘብና ከልብ በመቀበል እና በማመን ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጉድለቶች አሉበት ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:34 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG