በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲዝ ዋሺንግተን ዲሲ ናቸው


አቡነ ፍራንሲዝ ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው አንድሩስ የአየር ኃይል መደብ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ /ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ዓ.ም/
አቡነ ፍራንሲዝ ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው አንድሩስ የአየር ኃይል መደብ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ /ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ዓ.ም/

አቡነ ፍራንሲዝ ሊቀ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን ከዩናይትድ ስቴትሷ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው አንድሩስ የአየር ኃይል መደብ ዛሬ፤ ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ዓ.ም ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ ዋሺንግተን ዲሲ ሲደርሱ - ማክሰኞ፤ መስከረም 11/2008 ዓ.ም
አቡነ ፍራንሲዝ ዋሺንግተን ዲሲ ሲደርሱ - ማክሰኞ፤ መስከረም 11/2008 ዓ.ም

አቡነ ፍራንሲዝ ሊቀ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን ዛሬ፤ ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ዓ.ም ዋሺንግተን ዲሲ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል ቀድሞ ያልታየ ደማቅና የሞቀ እንደነበር ታዛቢዎች እየተናገሩ ነው፡፡

አቡኑ ከዩናይትድ ስቴትሷ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው አንድሩስ የአየር ኃይል መደብ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

“ለአባ ፍራንሲዝ ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገችው አቀባበል የአሜሪካ ሕዝብ ለእርሣቸው፤ ለትምህርቶቻቸው፣ ለእሴቶቻቸው እና ዕድሜአቸውን ለኖሩበት መንገድ ያለውን ያለውን አድናቆትና አክብሮት የሚያንፀባርቅ ነው” ብለዋል የዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የፕሬስ ኃላፊ ጃሽ ኧርነስት፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ ከአይሮፕላናቸው እንደወረዱ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት፣ ምክትላቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዋሺንግተንና በአካባቢዋ ያሉ ካቶሊካዊያን ሊቃነ-ጳጳሳትና ካቶሊክ ተማሪዎችም “ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንኳን ደኅና መጡ” እያሉ አስተናግደዋቸዋል፡፡

አቡነ-ፍራንሲዝ ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ባለፈው መጋቢትም ተገናኝተው የተወያዩ ቢሆንም የዩናይትድ ስቴትስን መሬት ሲረግጡ ግን የአሁኑ በሕይወታቸው የመጀመሪያቸው ነው፡፡

ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ አቡነ ፍራንሲን አንድሩስ አየር ኃይል መደብ ላይ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡
ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ አቡነ ፍራንሲን አንድሩስ አየር ኃይል መደብ ላይ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

“አቡኑ የሚያከብሯቸውን እሴቶች የሚሰብኩ ሳይሆኑ የሚኖሯቸው ሰው ናቸው” ብለዋል የዋይት ሃውሱ ጃሽ ኧርነስት በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው፡፡

ይህንን የአቡነ ፍራንሲዝን የዋሺንግተን ጉዞ ለማዘጋጀት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታዊ ቡድን ባለፈው ሰኔ ወደ ቫቲካን ተጉዞ እንደነበር ታውቋል፡፡

ነገ፤ ረቡዕ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በዋይት ሃውስ ቅጥር ግቢ ደቡባዊ መናፈሻ አሥራ አምስት ሺህ ታዳሚ በሚገኝበት እንኳን ደኅና መጡ ለማለት ይፋዊ ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱና ጳጳሱ በዚያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተናገሩ በኋላ ወደ ፕሬዚዳንቱ ገብተው ብቻቸውን ለውይይት እንደሚቀመጡ የወጣው መርኃግብር ያሳያል፡፡ ይህ ውይይት የፖለቲካ አጀንዳን የሚመክር ሳይሆን ለጋራ እሴቶች ያሏቸውን የቁርጠኝነት መግለጫዎች ለማጠናከር እንደሆነ የኦባማ አስተዳደር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

“ሁለቱም መሪዎች ሕይወቶቻቸውን ማኅበራዊ ፍትሕን ለማጠናከር፣ ተጠቃሚ ያልሆኑ ወገኖችን ዕድሎች ለማስፋት ስለመስጠታቸው ይመካከራሉ” ብለዋል ኧርነስት፡፡

በዋይት ሃውስ ባለሥልጣናት ማብራሪያ መሠረት የፕሬዚዳንቱና የጳጳሱ ውይይት ማኅበራዊና ምጣኔኃብታዊ አለመተካከልን፣ የአየር ንብረት ለውጥን መጋፈጥን የመሳሰሉ ነጥቦችንም ይዳስሳል፡፡

“ፓፓው የአምላክን ፍጥረት የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለብን ነግረውናል፤ ምክራቸው መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በተናጠል ለሚወስዷቸው የፖሊሲ ውሣኔዎች የሞራል ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡” ብለዋል የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪው ቤን ሮድስ፡፡

በመካከለኛው ምሥራቅ የእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ታጣቂዎች በኅዳጣን የእምነት ተከታዮች ላይ የሚያደርሷቸውን የበደልና የማዋከብ አድራጎቶች በተለይ ክርስቲያኖችና ያዚዲዎች ላይ የሚፈፅሟቸውን ግድያዎች ቀደም ሲል በይፋ አውግዘዋል፡፡

በአቡነ ፍራንሲዝ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ወቅት ከፕሬዚዳንቱና ሌሎቹም መሪዎች ጋር ከሚያነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢሚግሬሽን፣ የኢራን ኒኩሌር መርኃግብር ስምምነት፣ በዩናይትድ ስቴትስና በኩባ መካከል ያለው ግንኙነት መሻሻል ሊኖሩ እንደሚችሉ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

አቡነ ፍራሲዝ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታዊ ጉብኝታቸውን ለመጀመር ወደ ዛሬ፤ ማክሰኞ ዋሺንግተን ዲሲ የገቡት በኩባ ያደረጉትን ታሪካዊ የሦስት ቀናት ቆይታ እንዳጠናቀቁ ነው፡፡

አቡኑ በመጭው ሣምንት በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ መድረክ ላይ ወጥተው ለዓለም መሪዎች ንግግር እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡

ለተጨማሪና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያለውን የዋይት ኃውስ ቤተመንግሥት ዌብ ሳይት ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡

https://www.whitehouse.gov/campaign/pope-visit

ወይም ለትኩስ ዘገባዎች የቪኦኤን ሌሎች ሳይቶች ይጎብኙ፡፡

http://www.voanews.com/content/us-catholics-weigh-in-on-pope-francis-church/2972426.html

XS
SM
MD
LG