በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሚሊዮኖች እጣና ፈተና


 ስለ ፍልሰተኞችና ስደተኞችን በተመለከተ ከዓለም መሪዎች ጋር ያካሄዱት የጎን ስብሰባ
ስለ ፍልሰተኞችና ስደተኞችን በተመለከተ ከዓለም መሪዎች ጋር ያካሄዱት የጎን ስብሰባ

“ይህ ቀውስ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ እልቂትና ፍልሰት ነው።” ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን

ባለፈው ዓመት ብቻ ከ60 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተገደው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን አስታወቁ። ሁኔታው በእጅጉ ያሳሰባቸው መሆኑን የገለጡት ዋና ጸሀፊ ባን ኪሙን፣ በፍልሰት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በኒው ዮርክ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉቡኤ ትይዩ ትላንት አካሂደዋል።

“ይህ ቀውስ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ እልቂትና ፍልሰት ነው።”
ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን

በስብሰባው ከተሳተፉት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል በመንግስታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወርስ እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ይገኙበታል። ሳሌም ሰለሞን ከኒው ዮርክ ያጠናቀረችውን ዝርዝር ሄኖክ ሰማእግዜር አቀናብሮ አቅርቦታል። ዘገባውን ለመስማት፣ ይህንን ከታች ያለውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያድምጡ።

ከቀያቸው የተፈቀሉ ሚሊዮኖች እጣና ፈተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG