በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካቶሊኮች መሪ አባ ፍራንሲስ የስደተኞችን እግር በማጠብ ትህትና ሲያሳዩ

አቡኑ ጸሎተ ሃሙስ በዓል ሲከበር፤ በቤልጀምር ብራስልስ አሸባሪዎች ያደረሱትን ጥቃት ተንተርሶ፤ ጥቃቱን ለማውገዝ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችን እግር በትህትና አጥበዋል።

የሮማ ካቶሊክ ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ ትህትናን ለማሳየት በሚደረገው ተንበርክኮ እግር የማጠብ ስርዓት ስደተኞችና ከሌሎች ሀይማኖት የተውጣጡ ሰዎችን በማክበር እራሳቸውን ዝቅ አድርገዋል።

በደም የሚነግዱ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች፤ ፍላጎታቸው ሰላም ሳይሆን ጦርነት ነው። ወንድማማችነት አይሹም።
የሮማ ካቶሊክ ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ

አቡኑ ጸሎተ ሃሙስ በዓል ሲከበር፤ በቤልጀምር ብራስልስ አሸባሪዎች ያደረሱትን ጥቃት ተንተርሶ፤ ጥቃቱን ለማውገዝ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችን እግር በትህትና አጥበዋል።

አባ ፍራንሲስ ባደረጉት ንግግር የብራስልሱን ጥቃት አውግዘው፤ ከጥቃቱ ጀርባ ሰላም የማይፈልጉ የጦር መሳሪያ አምራቾች አሉበት ብለዋል።

"ከሶስት ቀናት በፊት የጦርነት ፍላጎት የተጠናወታቸው ሰዎች በአውሮፓ መዲና ጥፋት ፈጽመዋል። እነዚህ ሰዎች በሰላም ለመኖር የሚፈልጉ አይደሉም። ከዚህ ሁሉ ጀርባ ደግሞ የጦር መሳሪያ አምራቾች አሉ። በደም የሚነግዱ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች፤ ፍላጎታቸው ሰላም ሳይሆን ጦርነት ነው። ወንድማማችነት አይሹም።"ብለዋል።

አባ ፍራንሲስ በንግግራቸው የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች በሰላም እንዲኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የካቶሊኮች መሪ አባ ፍራንሲስ የስደተኞችን እግር በማጠብ ትህትና ሲያሳዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
የካቶሊኮች መሪ አባ ፍራንሲስ የስደተኞችን እግር በማጠብ ትህትና ሲያሳዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:48 0:00

XS
SM
MD
LG