ዋሽንግተን ዲሲ —
የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንስስ በአፍሪቃ ለመጀምርያ ጊዜ የሚያካሄድዱትን ኦፊሴላዊ ጉብኝት ነገ ረቡዕ ይጀምራሉ።
ኬንያን፣ ኡጋንዳንና የማዕከላዊ አፍሪቅ ሪፑብሊክን ይጎበኛሉ። ለሰብአዊ መብት የሚሟጎቱ ቡድኖች የርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳቱ ጉብኝት የፖለቲካ መብቶች እንዲከበሩ፣ የሀይማኖታዊ እምነት መቻቻል እንዲኖርና የአናሳ መብት እንዲከብር ጫና ያደርጋሉ ብለው ይጠብቃሉ።
በዩናትድ ስቴትስ ወደ 6,500 የሚሆኑ የውጭ ሃገር ተወላጆች የካቶሊክ ቄሶች ሲሆኑ፣ ከነዚህም ብዙዎቹ ከአፍሪቃ የመጡ ናቸው። አባ ይሳቅ መኮቮ ከኬንያ ነው ወደ አሜሪካ የመጡት። የቪኦኤዋ ካሮሊን ፕረሱቲ (Carolyn Presutti) ኬንያዊው አባ ጋር ያደረገችውን ቃለ ምልልስ አጠናቅራ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሃየ አርባዋለች። ሙሉውን ዝርዝር ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።