በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲስ ወደ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሲጓዙ እንዳይሰጉ ተባለ


በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ዋና ከተማዋ ባንግዊ(Bangui) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም ጠባቂ ወታደሮች
በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ዋና ከተማዋ ባንግዊ(Bangui) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም ጠባቂ ወታደሮች

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ያቀዱት ጉብኝት ለደህንነታቸውን አያሰጋም ተባለ።

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡን ፍራንሲስ ያቀዱት ጉብኝት ደህንነታቸውን አያሰጋም ሲሉ፥ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ፥ ወታደራዊ፥ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች ተናገሩ።

ይህ ያፍሪካውያኑ ባለሥልጣናት ማረጋገጫ የተሰጠው፥ ቫቲካን በጉብኝቱ ወቅት፥ ለአቡኑ ደህንነት ስጋቷን ካስተጋባች በሁዋላ ነው።

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ የሕዝብ ደህንነት ሚኒስትሩ ሲናገሩ፥ በቅርቡ ዋና ከተማዋ ባንግዊን (Bangui)ን ውስጥ ሁከት ተፈጥሮ እንደነበር ቢታወቅም፥ አሁን ጥበቃው ባስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡን ፍራንሲስ ባንግዊን (Bangui)ን ከአስራ አምስት ቀናት በሁዋላ በሚጎበኙበት ጊዜ፥ ምናልባት ተጨማሪ 850 የፀጥታ አስከባሪዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ የዓለሙ ድርጅት ህብረ ብሄር አረጋጊ ኃይል፥ በሃገሪቱ ብሄራዊ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው ከ 45 ቀናት በፊት፥ ተጨማሪ 750 ወታደሮችና 140 የፖሊስ መኮንኖች እንደሚመደቡ ይጠብቃል። ተጨማሪው ኃይል፥ ሁለት ዓመቱን በያዘው በዚያች ሀገር ቀውስ አሁን ያሉትን 10 ሺህ ወታደሮች ይቀላቀላል።

የአቡኑ ጉብኝት ለሀገሪቱ ቡራኬ ነው ሲሉ ተጠባባቂ ፕሬዘዳንቷ ካተሪን ሣምባ-ባንዛ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ያዳምምጡ።

አቡነ ፍራንሲስ ወደ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሲጓዙ እንዳይሰጉ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:15 0:00

XS
SM
MD
LG