ዋሽንግተን ዲሲ —
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የሮማውን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት አባ ፍራንሲስን በዋይት ሀውስ ውስጥ በኦፊሴል ተቀብለው አነጋገሩ። አምላካችን እግዚአብሔር የርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱን የፍቅርና የተስፋ መልዕክት በመስጠቱ፣ በአገራችንና በመላው ዓለም ያሉ ሕዝቦችን ማነቃቃቱ እንዴት ድንቅ ቀን ነው፣ በማለት ኃይለ-ቃል አሰምተዋል።
ዋይት ሀውስ እንደገለጸው፣ በአቀባበሉ ወቅት ፕሬዚደንት ኦባማ ስለ አቡኑን ሲናገሩ በዚህ ጉብኝትዎ ዙሪያ የሚገኘው ደስታ የሚመነጨው፣ እንደ ሊቀ-ጳጳስ ካለዎ ሚና ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ከሚያሳዩት ልዩ ባሕሪ ጭምር ነው ብለዋል።
እነዚህም ትህትናዎ፣ ውስብስብ ያልሆነውና ቀለል ያለ አቀራረብዎ፣ ከአንደበትዎ የሚወጡት እርጋታ የተመላባቸው ቃሎችዎና ለጋስ ቡራኬዎ ናቸው።
ሊቃነ-ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ በበኩላቸው፣ ዩናይትድ ስቴትስ በዓለማችን ያላትን ሚናና የምታበረክታቸውን አያሌ መልካም ነገሮች አወድሰው፣ በለሆሳስ ባሰሙት ቃል፣ "እግዚአብሄር አሜሪካን ይባርክ"ብለዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ፡፡