በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓፓው የመንግሥታቱ ድርጅት ንግግርና የኒው ዮርክ ቆይታቸው

አቡነ ፍራንሲዝ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ሲያደርጉ
አቡነ ፍራንሲዝ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ሲያደርጉ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚያደርጉትን ይፋ ጉብኝት አራተኛ ቀን ዛሬ ማለዳ የጀመሩት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ዛሬ ረፋዱ ላይ ለዓለም መሪዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን አቡነ ፍራንሲዝን ሲቀበሉ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን አቡነ ፍራንሲዝን ሲቀበሉ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚያደርጉትን ይፋ ጉብኝት አራተኛ ቀን ዛሬ ማለዳ የጀመሩት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ዛሬ ረፋዱ ላይ ለዓለም መሪዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ ባደረጉት ንግግር የዓለም ፕሬዚዳንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች የአየር ንብረት ለውጥን እንዲፋለሙ፣ ድኅነትን ለማጥፋት እንዲሠሩ፣ ግጭቶችን እየሸሹ የሚጓዙ ስደተኞችን ከጥቃት እንዲጠብቁና እንዲንከባከቡ አሳስበዋል፡፡

“ስግብግብና ገደብ የለሽ የሥልጣን ጥማት፣ ሃብት የማግበስበስና የብልፅግና ፍላጎት ያሉንን የተፈጥሮ ሃብቶችን ያለአግባብ መጠቀምን ያስከትልብናል፤ ደካሞችና የተገፉ ይበልጥ እንዲንገላቱ ያደርጋቸዋል” ብለዋል አቡነ ፍራንሲዝ፡፡

የሰው ልጅ በክብር እንዲኖር ቤተሰብ መመሥረትና መደገፍም እንዲችል መሠረታዊ ቁሣዊና መንፈሣዊ ፍላጎቶቹ እንዲሟሉለት እንደሚገባ አቡኑ መክረዋል፡፡

መሠረታዊ ቁሣዊ ፍላጎቶቹ መጠለያ ወይም መኖሪያ፣ ሥራ እና መሬት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

“መንፈሣዊ ፍላጎቶቹም የእምነት ነፃነትን፣ የትምህርትና ሌሎችም ሲቪል መብቶችን የሚያካትተው የመንፈስ ነፃነት ነው” ብለዋል አቡነ ፍራንሲዝ መሪዎቹ እንዲጠብቋቸው ሲጠይቁ፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ንግግራቸው በኋላ ወደ መስከረም 1/1994ቱ የሽብር ጥቃት ሥፍራ ሄደው የበርካታ ሃይማኖቶችን የፀሎት ሥነ-ሥርዓት መርተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG