በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባ ፍራንሲዝ ለአሜሪካ እንደራሴዎች ንግግር አደረጉ


በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሣት አቡነ ፍራንሲስ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤቱ ተገኝተው ለጥምር ጉባዔው ንግግር አድርገዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሣት አቡነ ፍራንሲስ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤቱ ተገኝተው ለጥምር ጉባዔው ንግግር አድርገዋል።

አባ ፍራንሲስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት ያሳለፉት መልዕክት በመካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች፣ የአየር ንብረት ለውጥና የካፒታሊዝም ሥርዓት ቅጥ ባጣ መልኩ መግዘፍን አስመልክቶ ነበር።

“በአንተ ላይ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ” የሚለውን “ወርቃማው ሕግ” ተብሎ የሚጠራውን የቅዱስ መፅሐፍን ጥቅስ አንስተው ሰፊ ንግግር አድርገዋል፡፡

በፖለቲካ ልዩነት የተከፈለው ኮንግረስ ዛሬ በአቡኑ መገኘት ለአፍታም ቢሆን አንድነት አሳይቷል።

በዚህ ሁኔታ በእጅጉ ከተደሰቱት መካከል አፈ ጉባዔው ጆን ቤነር ይገኛሉ፡፡ ቤነር እራሣቸው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ አባ ፍራንሲስን በክብር ተቀብለው አስተዋውቀዋቸዋል፡፡

የዛሬው የአቡነ ፍራንሲዝ ንግግር ለዩናይትድ ስቴትስ ህዝብ በቀጥታ የተላለፈ ሲሆን ለእንደራሴዎቹ፣ ለአሜሪካዊያንና ለዓለም ያስተላለፏቸው መልዕክቶች የገቢ አለመመጣጠን፣ የድህነት መስፋፋትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትሏቸው ችግሮች፣ የስደት ጉዳይ፣ ሠላምና ዓለምአቀፍ ትብብር፣ ፍቅርና መከባበር ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ዘጋቢዎቻችን ከየሥፍራው ያጠናቀሯቸውን ዘገባ የያዘውን ቅንብር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አባ ፍራንሲዝ ለአሜሪካ እንደራሴዎች ንግግር አደረጉ 5' 29"
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG