በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ርእሰ-ሊቃነ ዻዻሳት ፍራንስስ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ “ወሳኝ ሚና” እንድትጫወት ጥሪ አቀረቡ


ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥሪውን ያቀረቡት ከኢራኑ ፕረዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ጋር ዛሬ በቫቲካን ለአርባ ደቂቃዎች ያህል ዝግ ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስያን ርእሰ-ሊቃነ ዻዻሳት ፍራንስስ ኢራን “ወሳኝ ሚናዋን” ያሉትን በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማውረድ፣ የአሸባሪነት መስፋፋትንና የመሳሪያዎች ሽግግርን ለማቆም እንድትጠቀምበት ጥሪ አቅርበዋል።

ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥሪውን ያቀረቡት ከኢራኑ ፕረዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ጋር ዛሬ በቫቲካን ለአርባ ደቂቃዎች ያህል ዝግ ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

ከስብሰባው በኋላ የወጣ የቫቲካን መግለጫ ኢራን በመካከለኛ ምስራቅ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመፈለግ በተለይም አሸባሪነትንና የመሳርያ ሽግግርን ለማቆም “ያላት ጠቃሚ ሚና” ስላለው ጉዳይ አንስቷል።

ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሶስት አመታት በፊት ገደማ ከተመረጡበት ጊዜ አንስቶ ግጭቶችን ለመፍታት የሚያስችለው ተመራጭ መንገድ መነጋገርና ሽምግልና ነው በሚለው ነጥብ ላይ ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል።

እአአ ከ 1999 ዓ.ም. ወዲህ ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳትና የኢራን መሪ በቫቲካን ተገናኝተው ሲነጋገሩ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። አንድ የኢራን መሪ ቫቲካንን ሲጎበኝ ደግሞ ለሀያ አመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ የመጀመርያው ነው።

ሩሃኒ በኢጣልያና በፈረንሳይ የአራት ቀናት ጉብኝት ያካሄዱት ከስድስት ሀገሮች ጋር የተደረገው የኑክልየር ስምምነት ከተተገበረ ወዲህ ከቀድሞ አጋሮች ጋር የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ታይቷል።

በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከተነሳ ወዲህ ሩሃኒ በውጭ ማዋዕለ-ነዋይ ላይ ትኩረት እየጣሉ መሆናቸው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG