በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲዝ የአየር ንብረት አቋም - ትንታኔ


አቡነ ፍራንሲዝ ለዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ባደረጉበት ወቅት
አቡነ ፍራንሲዝ ለዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ባደረጉበት ወቅት

መሬት ሥጦታችን ናት፤ ልንጠብቃት ይገባል ብለዋል፤ አቡነ ፍራንሲዝ ርዕሰ - ለቃነ ጳጳሣት ዘካቶሊካዊያን፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ እና ፕሬዚዳንት ኦባማ በዋይት ሃውስ
አቡነ ፍራንሲዝ እና ፕሬዚዳንት ኦባማ በዋይት ሃውስ

አቡነ ፍራንሲዝ የአየር ንብረት አቋም - ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

መሬት ሥጦታችን ናት፤ ልንጠብቃት ይገባል ብለዋል፤ አቡነ ፍራንሲዝ ርዕሰ - ለቃነ ጳጳሣት ዘካቶሊካዊያን፡፡

አቡነ ፍራንሲዝ ይህንን ከሌሎች አንድም “የአየር ንብረት ለውጥ የሚባል ክስተት የለም” ከሚሉ በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በምድራችን ላይ የሚታዩ የድርቅ፣ የማዕበል፣ የጎርፍና የቃጠሎ ክስተቶች “የአየር ንብረት ለውጥ ስላለ ሳይሆን የፈጣሪ ቁጣ ነው” ከሚሉ የሃይማኖት መሪዎችና አንዳንድ ፖለቲከኞች ፈፅሞ የሚለያቸውን አቋማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊትም በይፋ አሳውቀው ዓለምን አስገርመዋል፡፡

አቡኑ ይህንኑ አቋማቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸው ወቅትም ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቤተመንግሥታቸው በክብር በተቀበሏቸው ወቅትና በሃገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት ጥምር ጉባዔ ላይም ቀርበው ባደረጓቸው ንግግሮች እያስረገጡ አስገንዝበዋል፤ ለተፈጥሮ ጥበቃ እንዲደረግም ተማፅነዋል፡፡

ይህንን የአቡኑንና የቫቲካንን የዘንድሮ አቋም፤ አቋማቸው በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ላይ ያለውን አንድምታ አስመልክቶ በተፈጥሮ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የሚመራመሩትን ሳይንቲስትና ካናዳ በሚገኘው ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የልማትና የምርት ሂደት ቡድን ሊቀመንበር ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ ለቪኦኤ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG