በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲስ የኣፍሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን እየተመለሱ ናቸው


የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ሶስት ሃገሮች የጎበኙበትን የመጀመሪያ የኣፍሪካ ጉዞኣቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን እየተመለሱ ናቸው።።

ብጹዕ ኣቡነ ፍራንሲስ የሰላምና የመልሶ ዕርቅ መልዕክታቸውን ያሰሙት ዋና ከተማዋ ባንጊ ፒኬ5 በሚባለው ቀበሌ ባለ መስጊድ ሲሆን ባንድ ወቅት ብዙ ሺህ ይኖሩበት የነበረው ያ ቀበሌ በተደጋጋሚ የክርስቲያንና ሙስሊም ሚሊሺያዎች ግጭት አምባ ሆኖ ቆይቱዋል። የሚበዙት የፒኬ 5 ነዋሪዎች ወደሊሌሎች ከተሞች ተሰደዋል አልያም በየተፈናቃይ ካምፖች ተጠልለዋል።

በኣካባቢው ጸጥታ ስጋት ቢኖርም አቡኑ በዘቦችና በተባበሩት መንግሥታት ሰላም ኣስከባሪዎች ታጅበው መስጊዱ የደረሱት በግልጹዋ ተሽከርካሪያቸው በ"ፖፕሞቢልዋ” ሆነው ነው።

ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ውንድማማች ናችው፡ አብረው መኖር የማይችሉበት ምክንያት የለም ብለዋል።

“ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች እንዲሁም የባህላዊ ዕምነቶች ተከታዮች ለአያሌ ዓመታት አብረው ኖረዋል። ናቸው። አንድ ላይ ሆነን ፡ ጥላቻን፡ ቂም በቀልን፡ ሁከትን በተለይ ደግሞ በሃይማኖትና በራሱ በእግዚኣብሄር ስም የሚካሄድ ሁከትን ዕምቢ ማለት ኣለብን።” ብለዋል።

“በፖለቲካ ምክንያትና በክርስቲያንና ሙስሊም ሚሊሺያዎች ግጭት ስትታመስ በቆየችው ሀገር ጉብኝቴ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ካልተገናኘሁ የተሙዋላ አይሆንም” ብለዋል።

አሊ አይቻቱ በመስጊዱ ግቢ በድንኩዋን ከተጠለሉት ብዙ መቶ ተፈናቃዮች አንዱዋ ናቸው። እአአ ባለፈው 2014 ዓም መጀመሪያው ላይ ብጥብጡ በጋመበት ወቅት ነው ከመኖሪያቸው የተሰደዱት።

“አቡኑ ሲመለሱ ሰላም ባይወርድ መንግሥት ሰላም እንዲወርድ የተጀመርውን ስራ ይቀጥለዋል ብዬ ኣምናለሁ በመንደራችን ውስጥ የምንደርስበት አጥተን ተጠምደን ነው

ያለነው። እና ኣሁንም ሰላም የማይወርድ ከሆነ እግዚኣብሄርን መለመን ብቻ ነው። ሌላ ምን አደርጋለሁ” ሲሉ ነው የተሰሙት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባንጉዊ ብሄራዊ ስቲዲየም ለተሰባሰቡ እጅግ ብዙ ምዕመናን ስርዓተ ቅዳሴ በማካሄድ ነው የኣፍሪካ ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁት። ተፋላሚዎቹ ወገኖች ትጥቃቸውን እንዲፈቱና የሃይምኖት ግጭቱን ለማስቆም የሚደረጉትን ጥረቶች እንዲያግዙ ተማጽነዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ካትሪን ሳምባ ፓንዛ (Catherine Samaba Panza) ቀደም ብለው በብጹዕነታቸው ጉብኝት ዋዜማ ሲናገሩ ኣቡኑን የሰላም መልእክተኛ ኣድርጎ እንደሚመለከታቸው ጉብኝታቸው ህዝቡ አንዱ ሌላው ተቀብሎ እንዲኖር በአንድነት ጥረት እንዲያደርግ የሚቀሰቃስ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ኣሁንም ጥያቄው ጉብኝታቸው ውጥረቱን ለምርገብ ረድቱዋል ወይ የሚለው ነው። ከ2013 ዓመተ ምህረት መጀመሪያ ወራት አንስቶ ሲቀጣጠል የቆየው የመካከለኛ ኣፍሪካ ሪፑብሊክ ግጭት በሺዎች የተቆጠረ ህዝዝብ ኣልቆበታል። ከኣንድ ሚሊዮን በላይ ከመኖሪያው ተፈናቅሉዋል።

ናሰል ደሉርደ (Nancelle Delourde) ብጹዕነታቸው በባንጊ በደረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ከተገኘው ህዝበ ክርስቲያን ኣንዱዋ ናቸው። ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ኣብረው ኣብረው የሚኖሩበት ዘመን ተመልሶ እንዲመጣ ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

“ትንሽ ይከብዳል። ግን ሁላችንም የእግዚኣብሄር ፍጡራን ነን። ስለዚህ ለዕርቀ ሰላም ዝግጁ ነን።” ሲሉ ነው የተሰሙት ።

ለመካከለኛ ኣፍሪካ ሪፑብሊክ ቀጣዩ የሰላም ፈተና እ ኤ አ በመጨው ታህሳስ ኣስራ ሶስት ይሆናል። የዚያን ዕለት በህገ መንግስቱ ላይ ውሳኔ ህዝብ ይካሄድና ከዚያም ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ዕቅድ ተይዙዋል።

ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁት በማዕከላዊ ኣፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጊ ኣንድ መስጊድ ከጎበኙ በሁዋላ ነው። ክሪስ ስትየን (Chris Stein) ከባንጊ ለቪኦኤ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ ይዛዋለች። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ኣቡነ ፍራንሲስ የኣፍሪካ ጉዞኣቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን እየተመለሱ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00

XS
SM
MD
LG