በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባ ፍራንሲስ የኬንያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ፤ ዩጋንዳ ገቡ

  • ቪኦኤ ዜና

አቡነ ፍራንሲስ በኬንያ ጉብኝታቸው ወቅት

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የናይሮቢ ጉብኝታቸውን ያጠቃለሉት አንድ የተጎሣቆለ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች መኖሪያ ሠፈር ተመልክተው ነው።

የአባ ፍራንሲስ የኬንያ ጉዞ

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የናይሮቢ ጉብኝታቸውን ያጠቃለሉት አንድ የተጎሣቆለ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች መኖሪያ ሠፈር ተመልክተው ነው።

በዚያም ዝቅተኛ ኑሮ በሚኖሩ የከተማይቱ ድሃ ዜጎች ላይ ይፈፀማል ያሉትን “ግፍ” አውግዘዋል።

ለችግሩ ምክንያት ሆነዋል በማለት የከሰሷቸው የሕዝቡን ሃብት አጋብሰው ሥልጣን ላይ የቆዩ “ስግብግቦች” ሲሉ የጠሯቸውን “ጥቂቶች”ን ነው።

አቡነ ፍራንሲስ የኬንያ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ዛሬ ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የገቡ ሲሆን ነገ በዩጋንዳ ሰማዕታት ቤተ መቅደስ ሕዝባዊ የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ይመራሉ፡፡

አቡነ ፍራንሲስ በኬንያና በዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል አብረው እየተጓዙ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG