በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማዉ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የአሜሪካ ጉብኝታቸዉን አጠናቀዋል


የሮማዉ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የተለያዩ ቤተሰብና ማህበረሰብ እንዲሁም በመተሳሰብና መተዛዝንን ዙሪያ ያጠነጠኑ ንግግሮችን አስምተዉ የአሜሪካ ጉብኚታቸዉን አጠናቀዋል።

ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንስስ በፊላዴልፊያ ጉብኝቻቸዉ ትላንት እሁድ ማለዳ ላይ ካረፉባቸዉ አቡኖች እጅግ ሞቅ ያለ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አባ ፍራንስ ቀድም ብሎ በካቶሊክ ቀሳዉስት የጾታ ጥቃት ከደረሰባቸዉ አምስት ሰዎች ጋር በግል ተገናኝተዋል።

በተለይ የጾታ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሰዎች ቫቲካን ይህን ለረጅም ዓመታት ቀሳዉስት ያደረሱትን በደል ችላ ከማለት ሌላ በቂ እርምጃ አልወሰደችም በማለት ይከሳሉ። ሆኖም እሁድ ለት ጥቂቱቹ የጥቃቱ ሰለባዎች ካነጋገሩ በሁዋላ ርእስ ሊቃነጳጳሳት ፍራንስ ማንም ህጻናትን በጾታ አጥቅቶ ቢገኝ እንደማይታለፍና ተጠያቂ እንዲመሆን ተናግረዋል።

የቪኦኣኤዉ ሮበርት ራፋኣኤል(Robert Raffaele) አቡኑ ትላንት ማለዳ በፔንስልቫኒያ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ያከናወኑዋቸዉን አጠናቅሯል ፣ ትዝታ በላቸዉ ያቀናበረችውን ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የሮማዉ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ የአሜሪካ ጉብኝታቸዉን አጠናቀቁ 3’53”
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG