በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መተማ ስለተያዙት ተሳቢዎች በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ምንም እንደማያውቁ ገለፁ


ፎቶ፡ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኘ በመተማ እንዲቆሙ ከተደረጉት የጭነት ተሽከርካሪዎች አንዱ
ፎቶ፡ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተገኘ በመተማ እንዲቆሙ ከተደረጉት የጭነት ተሽከርካሪዎች አንዱ

የመተማ ዮሃንስ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩ “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል - ምዕራብ ጎንደር ብርጌድ አዣዥ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ አስታወቁ።

መተማ ስለተያዙት ተሳቢዎች በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ምንም እንደማያውቁ ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:28 0:00

መነሻና መድረሻቸው የት እንደሆነ ለጊዜው ያልተገለፀው አምስቱ ባለተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪዎች ድንበሩን ከማለፋቸው በፊት መተማ ዮሃንስ ላይ የተያዙት የአካባቢው ወጣቶች መንገድ ዘግተው ካስቆሟቸው በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ማንኛውም ድንበር የሚያቋርጥ የመከላከያም ሆነ ሌላ ማጓጓዣ እንቅስቃሴ መረጃ ወትሮ ቀድሞ እንደሚደርሳቸው ለቪኦኤ የገለፁት በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የ33ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ብርጌድ፣ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ኮለኔል ሸዋገኝ አብዬ አሁን ስለተያዙት አምስት ተሽከርካሪዎች ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ጉዳዩ በፖሊስና በመከላከያ ኃይሉና አጠቃላይ አካባቢው ላይ ባለ የፀጥታ ኃይል በጥምር እየተመረመረ መሆኑንም ሁለቱም አዛዦች ገልፀዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG