በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ልጆቻችን ስለመለቀቃቸው ያወቅነው ነገር የለም” - ቤተሰቦች


dembidolo University
dembidolo University

ከአንድ ወር ተኩል በፊት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ “በታጣቂዎች ታገቱ” ከተባሉ ተማሪዎች ውስጥ የተወሰኑት ወላጆች ፤ ልጆቻቸው ከታገቱ ጀምሮ መፍትሔ ለማግኘት ያህል በመንከራተት ላይ እንዳሉ ገልፀው ስለመለቀቃቸውም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አነዲት ከመታገት አምልጬ ወጥቻለሁ ያለች ተማሪ በበኩሏ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አባት ሸሽገው ለፖሊስ እንዳስረከቧት ገልፃ ስለጓደኞቿ መታገት ለአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ክፍል እና ለተማሪዎቹ ወላጆች ማሳወቋን ገልፃለች።

በዚህ ጉዳይ ላይ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአሁኑ ሰዓት አምስት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና አንድ ሌላ ተማሪ በአጠቃላይ ስድስት ተማሪዎች

በእገታ ላይ መሆናቸውን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደም የታገቱ 13 ሴቶችና ስምንት ወንዶች በድምሩ 21 ልጆች በሰላማዊ ሁኔታ መለቀቃቸውንም ገልፀዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

“ልጆቻችን ስለመለቀቃቸው ያወቅነው ነገር የለም” - ቤተሰቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:06 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG