በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመላው ዓለም የሚገኙ ስደተኞችን ለማቋቋም ዓለም ቃል ገብቷል


ከደቡብ ሱዳን ተሰደው ጋምቤላ ውስጥ በሚገኝ ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች። ፎቶ ( UNHCR)
ከደቡብ ሱዳን ተሰደው ጋምቤላ ውስጥ በሚገኝ ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች። ፎቶ ( UNHCR)

ከታኅሣሥ 6 እስከ 8/ 2012 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ከመላው ዓለም የተውጣጡ ስደተኞችና 750 ልዑካን ቡድን አባላትን ጨምሮ ወደ 3ሺሕ ሰዎች ጀኔቫ ውስጥ በዓለም ላይ ስላሉ ስደተኞች ለመምከር፣ ሐሳብ ለመለዋወጥ እና የገንዘብና የዓይነት እና የስልት የእርዳታ ቃሎችን ለማሰባሰብ ተቀምጠው መክረዋል።

ይህ Global Refugee Forum ወይም "ዓለምአቀፍ የስደተኞች ጉባኤ” የተዘጋጀው ዓምና በታኅሣሥ ወር 2011 ዓ.ም በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የፀደቀውን global refugee compact ሰነድን ተከትሎ የተዘጋጀ ነው።

በዚህ ጉባኤም ላይ በጦርነትና በተለያየ ምክኒያት አገራቸው ለቀው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ጥገኝነት ጠይቀው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ዜጎች ባሉበት ተምረውና ሰርተው ሕይወታቸውን መቀየር የሚችሉበት ሁኔታ ውይይት ተደርጎበታል።

ጽዮን ግርማ ከዚህ ውይይት ጋር የተያያዘ ዘገባ አሰናድታለች። ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ተሰዳ የጥገኝነት ጥያቄዋ መልስ እስኪያገኝ በመጠባበቅ ላይ ያለች ስደተኛም በስልክ አነጋግራለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በመላው ዓለም የሚገኙ ስደተኞችን ለማቋቋም ዓለም ቃል ገብቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:00 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG