በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኢትዮጵያን እናድን" - ውይይት


የ “የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ -(ኢዜማ) ዋሽንግተን ዲስ የድጋፍ ማኅበር ” ከ“እኛ ነን ኢትዮጵያ ስብስብ” ጋር በትብብር “ኢትዮጵያን እናድን” በሚል ርእስ ባዘጋጁት በዚህ ውይይት ሐሳብ አቅራቢዎች።
የ “የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ -(ኢዜማ) ዋሽንግተን ዲስ የድጋፍ ማኅበር ” ከ“እኛ ነን ኢትዮጵያ ስብስብ” ጋር በትብብር “ኢትዮጵያን እናድን” በሚል ርእስ ባዘጋጁት በዚህ ውይይት ሐሳብ አቅራቢዎች።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ የተወሳሰበ በመሆኑ የሚያስፈልጋትም የተወሳሰበው የሚፈታ፣ ጠንካራና የተጠና መፍትሔ ሊሆን እንደሚገባው በዋሽንግተን ዲሲ ለውይይት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ገለፁ።

የ “የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ -(ኢዜማ) ዋሽንግተን ዲስ የድጋፍ ማኅበር ” ከ“እኛ ነን ኢትዮጵያ ስብስብ” ጋር በትብብር “ኢትዮጵያን እናድን” በሚል ርእስ ባዘጋጁት በዚህ ውይይት፤ ከሌሎች የሚማር ማኅበረሰብ ብልህ በመሆኑ ክፉ ነገር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንዳይደርስ ከሩዋንዳ መማር ያስፈልጋል የሚል ሐሳብ ከትንታኔ ጋር ቀርቧል።

አደጋውን ለመቀነስና ለውጥ ለማምጣትም የኢትዮጵያ ችግርን በተጠና መልኩ ለይቶ በሚደረግ ውይይት ወደ መፍትሔ ማምራት ይሻልል ብለዋል። ለዚህም ምሑራን ዋናውን ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው በውይይቱ ወቅት የተነሳ ነጥብ ነው። የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብም የችግሩን አሳሳቢነት በሚገባ በመረዳት አገር በማዳን ተግባር ውስጥ ሊሰማራ ይገባል ብለዋል። ብሔርተኝነትም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

ውይይቱን የተከታተለችው ጽዮን ግርማ ከውይይቱ የተወሰነውን ክፍል በአጭሩ አሰናድታዋለች።

"ኢትዮጵያን እናድን" - ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:43 0:00


ውይይቱ ሰፋ ያለ በመሆኑ በዚህ አጭር ክፍል ሁሉም መካተት አልቻለም። ነገር ግን ቀሪውን ዘገባ በእሁድ ምሽት ዝግጅታችን ይቀርባል። በድረ ገፃችን እና በፌስ ቡክ ገፃችን ላይም በምስል ጭምር ታገኙታላችሁ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG