በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምስራቅ ኦሮሚያ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ


በምስራቅ ሐረርጌ ሁለት አብያተ ክርስቲያን እና የክርስትና እምነት ተከታይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ በምዕራብ ሐረርጌ ደግሞ አንዲት ሴት መገደሏን እና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በቡድን በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች መሆኑንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና የካቢኔ አባላት ጋር አስቸኳይ ውይይት ለማድረግ መወሰናቸውን መንበረ ፓትርያርክ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።
በሌላ በኩል የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አድራጎቱን አገር የማተራመስ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች የሚፈፅሙት ነው፤ ከአገር የሚበልጥ ነገር ስለሌለም አገር እንዳትፈርስ ጠንክረን እንሰራለን” ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደግሞ “መንግሥት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሌት ተቀን እየሠራ ነው” ብለዋል። (ጽዮን ግርማ ያሰናዳችውን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ)

የምስራቅ ኦሮሚያ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:30 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG