በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የጋዜጠኝነት ሞያ ከሰብዓዊ መብት ትግልና ከፖለቲካ ሥራ ጋር ተዳብሎ አንድ ላይ መተግበር የሚችል ነው ወይ?” በሚል ጥያቄ ዙሪያ የተደረገ ውይይት።


እስክንድር ነጋ በሕትመት ጋዜጠኝነት ለረጅም ዓመታት ሠርቷል። በሰርካለም አሳታሚ ይታተሙ የነበሩ ምንሊክ፣ አስኳል እና ሳተናው ጋዜጦችን ያዘጋጅ ነበር። ከስምንት ጊዜ በላይ ለእስር ተዳርጓል። ከስድስት በላይ ሐሳብን ከመግለፅና ከመጻፍ ነፃነት ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀብሏል። አሁን የኢትዮጲስ ጋዜጣ ባለቤት ነው። ከአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የባላደራ ምክርቤትም ሰብሳቢ ነው።

XS
SM
MD
LG