በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦች ተናገሩ


ደምቢ ዶሎ
ደምቢ ዶሎ

ከአንድ ወር ተኩል በፊት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ “በታጣቂዎች ታገቱ” ከተባሉ ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ውስጥ ሃያ አንዱ መለቀቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይፋ ቢደረግም ልጆቻቸው የታገቱባቸው ቤተሰቦች ግን እስካሁን ምንም የሰሙት ነገር አለመኖሩን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች አሁን በመንግሥት እጅ መሆናቸውን ገልፀው፤ ቀሪዎቹን ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። እገታው የተፈፀመውም የ“ኦነግ ሸኔ” ተብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች መሆኑን ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:10 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG