በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ለእርዳታ የተላከውን እህል ለማዳበርያ ክፍያ እየሸጡት ነው ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ይከሳሉ


አቶ ገብረእግዝአብሔር ወልደገብርኤል የራያ አላማጣ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ገብረእግዝአብሔር ወልደገብርኤል የራያ አላማጣ ዋና አስተዳዳሪ

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው መረጃው እንደደረሳቸው ገልፀው፤የገጠር አስተዳዳሪዎችን ጠይቀው ድርጊቱ አለመፈፀማቸውን እንደነገርዋቸው ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል በራያ አላማጣ ወረዳ የገጠር ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ለእርዳታ የተላከውን እህል ለማዳበርያ ክፍያ እንዲውል በጨረታ እየሸጡት ነው ሲሉ ያከባቢው ነዋሪዎች ይከሳሉ።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብረእግዝአብሔር ወልደገብርኤል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው መረጃው እንደደረሳቸው ገልፀው፤የገጠር አስተዳዳሪዎችን ጠይቀው ድርጊቱ አለመፈፀማቸውን እንደነገርዋቸው ገልፀዋል።

ቢሆንም ግን አሁንም ከናንተ ያገኘነውን መረጃ መሰረት በማድረግ ህብረተሰቡን በመጠየቅ መጣራት ያለበት ነገር ካለ እናጣራለን፤ ድርጊቱን የፈፀመ ካለም ህጋዊ እርምጃ እንወስድበታለን ብለዋል።

ዘጋብያችን ግርማይ ገብሩ ወደ አከባቢው በመሄድ ጥቆማውን ያቀረቡትንና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጠይቆ የሚከተለውን ልዩ ዘገባ ልኳል።

XS
SM
MD
LG