በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፋሲካ በዓል አከባበር በትግራይ


የደሮ ገበያ በመቐለ /ፎቶ - ግርማይ ገብሩ/
የደሮ ገበያ በመቐለ /ፎቶ - ግርማይ ገብሩ/

የገበያው ሁኔታ በተለይም የደሮ፣ የበጎችና የፍየሎች ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ዝቅተኛው የደሮ ዋጋ 100 ብር፣ ከፍተኛው 250 ብር መካከለኛው ደግሞ 150 ብር እንደተሸጠ ሸማቾች ይነገራሉ። ፍየል ትልቁ እስከ 5000 ብር ደርሷል።

በትግራይ ክልል የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በዓሉን እንደ አቅማቸው ለማክበር ሽርጉድ ሲሉ ነው የሰነበቱት። በጣም ብዙ ሰዎች ከሚሰሩበት ቦታ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመምጣት በዓሉን የማክበር ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

የበጎች ገበያ በመቐለ
የበጎች ገበያ በመቐለ

ይህ በእንዲህ እያለ የገበያው ሁኔታ በተለይም የደሮ፣ የበጎችና የፍየሎች ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ዝቅተኛው የደሮ ዋጋ 100 ብር፣ ከፍተኛው 250 ብር መካከለኛው ደግሞ 150 ብር እንደተሸጠ ሸማቾች ይነገራሉ። ፍየል ትልቁ እስከ 5000 ብር ደርሷል። በአንፃሩ የበሬ ዋጋ ካለፈው ዓመት የተለየ ጭማሪ አላሳየም፤ እንድያውም ተረጋግቷል፤ ከፍተኛ ዋጋው 12 ሺህ ብር ነው ብሏል አስተያየት ሰጪዎች።

ግርማይ በከተማዋ በመዘዋወር መንገድ ላይ ከሚለምኑት የኔ ብጤዎች እስከ ባለ ምግብ ቤቶች የፋሲካን በዓል እንዴት ለማክበር እንደተዘጋጁ ጠይቋል። ሁሉም ለፋሲካ በዓል ልዩ ክብር ሰጥተው በደማቅ ሁኔታ እንደሚያከብሩት ገልፀው፤ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ዕለት የታመሙት፣ የተቸገሩትና የታሰሩት ወገኖቻችን ካልጠየቅንበትና ያለንን ተካፍለን ካላሳለፍነው በዓሉ ከሌላው ቀን የተለየ ትርጉም አይኖረውም ሲሉ ይናገራሉ።

ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

የፋሲካ በዓል አከባበር በትግራይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG