መቀሌ —
በትግራይ ክልል በ1999 ዓ.ም. በ15 በደማቸው ውስጥ ኤች አይቪ ቫይረስ ያላቸው ሴቶች የተቋቋመው ማኅበር በአሁኑ ሰዓት 1,350 አባላት አሉት። ማኅበሩን ካቋቋሙት ሴቶች አንዷ ወይዘሮ መልክዓ አስገዶም ይባላሉ፤ በአሁኑ ሰዓት ማኅበሩን በሊቀመንበርነት ይመሩታል።
የማኅበሩ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ የታመሙትን በነፃ ፈቃዳቸው ለመንከባከብ በሚያደርጉት ጥረት ሌላው ቀርቶ ለሳሙና መግዣ እንኳን እንደሚቸገሩ ወይዘሮ መልክዓ ይናገራሉ።
በአሁኑ ሰዓት ወጣቱ ራሱን እየጠበቀ አይደለም ያሉት ወይዘሮ መልክዓ መንግስትና ሕብረተሰቡ ዋል እደር ሳይሉ ፊታቸውን ቫይረሱን ለመከላከል ወደ ሚደረገው ጥረት ብያዘሩ ይሻላል ሲሉም ያሳስባሉ።
ግርማይ ገብሩ ሊቀ መንበሯን ራሳቸውንና ማኅበራቸውን እንድያስተዋውቁ ጠይቋቸው በሚሰጡት መልስ ላይ የተካሄደ ቃለ-ምልልስ አለ፣ ከድምፅ ፋይሉ ያድምጡ።