በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ የእምባስነይቲ ህዝብ ቅሬታውን በሰልፍ ገለፀ


መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።

መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

ህዝቡ የፍርድ ቤት ፋይል ለመክፈት የሚከፍለውን 50 ሳንቲም ለመክፈል በሚኒባስ 34 ብር ከፍሎ ወደ የወረዳው ማእከል ዕዳጋ ዓርቢ እንደሚጓዝ በዚህም ምክንያት በኢኮኖሚያዊ ችግርና በመልካም አስተዳደር እጦት እንደተሰቃየ ገልጿል።

የቀድሞ ወረዳው እንዲመለስለትና መንግስት በቅርብ እንዲያስተዳድረው በተወካዮቹ በኩል ወደ ክልላዊ መንግስት 14 ጊዜ ወደ ፌዴራሉ መንግስት ደግሞ አንድ ጊዜ መጠየቁን በሰለማዊ ሰልፉ ወቅት ተገልጿል።

ቢሆንም የፌደራሉ መንግስት ተወካይ ድሮውም ለናንተ እንዲመች ብለን ነበር ያደረግነው የማይመቻችሁ ከሆነ ግን እንነጋገርበታለን ብለውናል ይላሉ፤ በአንፃሩ ደግሞ የክልሉ መንግስት ጥያቄው ዛሬም ነገም እንደማይመለስ ነገሩን ይላሉ አቶ ዘርኡ ኪዳኑ።

ህዝቡ ከወከላቸው አንዱ አቶ አብርሃ ገብረመስቀል ባለፈው ሚያዝያ 9 ወደ አከባቢው የተጓዘው የወረዳው፣ የዞኑና የክልሉ የባለስልጣናት ቡዱን ከህዝቡ ከተውጣጡት 220 ሰዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ጥያቄው የህዝብ ጥያቄ እንደሆነ አረጋግጠዋል ቢሆንም ባለስልጣናቱ የናንተን ጥያቄ ከመለስን ሌሎች አካበቢዎችም ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀርቡብናል በሚል ጥያቄያችንን ውድቅ አድርገውብናል ሲሉ ተናግሯል።

በትግራይ የእምባስነይቲ ህዝብ ቅሬታውን በሰልፍ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:41 0:00

የህዝቡ ተወካይ መድረክ ላይ ባሰሙት የአቋም መግለጫ አሁንም መንግስት የህዝቡን ጥያቄ እንዲመልስ ጥሪ አቅርበው ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሌላ አከባቢ በመሄድ እንደማንተዳደር እናሳውቃለን ሲሉ ገልጿል። በመጨረሻም መንግስት ህዝቡ ያቀረበውን የመብት ጥያቄ ካልመለሰ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸው ሰዎች ውክልናችንን ማንሳታችን በይፋ እንገልፃለን በሚል ውሳኔያቸውን በመግለጫቸው በኩል አቅርበዋል።

ትላንት በነበለት ከተማ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የተገኘው ግርማይ ገብሩ ለዛሬ ልዩ ዘገባ ልኳል።

በትግራይ የእምባስነይቲ ህዝብ ቅሬታውን በሰልፍ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG