በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ከሚኖር ህዝብ ግማሹ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አላገኘም


በትግራይ ክልል ራያ ዓዘቦ ከፍተኛ ድርቅ እና የምግብ እጥረት
በትግራይ ክልል ራያ ዓዘቦ ከፍተኛ ድርቅ እና የምግብ እጥረት

በትግራይ ክልል በራያ ዓዘቦ ወረዳ የሚኖር ህዝብ ለከባድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ተጋልጠናል ይላል።

ይህንን ችግር ለማቃለል የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶችም አገልግሎት መስጠት እንዳልጀመሩ ህዝቡ ይናገራል።

በወረዳው በሐደ አልጋ ቀበሌ በዳላተ የገጠር መንደር የሚኖሩ አቶ ሕሉፍ ገብረሚካኤልና ጎረቤቶቻው በንጹህ የመጠጥ ውሃ እጦት እንደተሰቃዩ በአጽንኦት ገልፀዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ክፍሎም ሃይለ ከህዝቡ እየቀረበ ያለው ቅሬታ ትክክል መሆኑን አምነው እንድያውም ግማሹ የወረዳው ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኝ ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት መንግሥት ሦስት የመፍትሄ መንገዶችን የጠቆሙት አቶ ክፍሎም ጊዜያዊ ውሃ በቦቴ ማከፋፈል፣ ሌላው የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ውሃ ለህዝቡ ማቅረብ እንዲሁም የውሃ ቧምቧ መሥመር በመዘርጋት እንደሆነ ዘርዝረዋል።

ዘጋብያችን ግርማይ ገብሩ ወደ አከባቢው በመጓዝ ሕዝቡንና አስተዳደሩን አነጋገሯል። ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ከሚኖር ህዝብ ግማሹ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አላገኘም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


በተጨማሪም ከቦታው የተላኩ ፎቶዎችን ከዚህ በታች ያገኛሉ።

XS
SM
MD
LG