በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ


በኢትዮጵያ የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ (ALFA) የተሰኘ የትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች ክፍል ውስጥ
በኢትዮጵያ የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ (ALFA) የተሰኘ የትምህርት መርሃ ግብር ተማሪዎች ክፍል ውስጥ

በኢትዮጵያ የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ (ALFA) የተሰኘ የትምህርት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

የትምህርት መርሃ ግብሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ከ2011 ጀምሮ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ በትግራይ ክልል ተግባራዊ መሆኑን ታውቋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን የትምህርት መርሃ ግብር ከሚያካሂዱት ድርጅቶች አንዱ “Operation Rescue Ethiopia” ይባላል፤ ወላጆቻቸውን በኤች አይ ቪ ኤይድስ ያጡና ጧሪ የሌላቸው ህጻናትን የሚንከባከብ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው።

የድርጅቱ የበላይ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ተስፋይ የትምህርት መርሃ ግብሩ የትና ልምን እንደተጀመረ ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

"ALFA በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ነው የተጀመረው፤ ዋናው ዓላማው በተላያየ አጋጣሚ ወደ ትምህርት ገበታ ያልመጡ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 የሆኑ ገጠር ውስጥ የሚኖሩ ህጻናትን ወደ ትምህርት ዓለም ማምጣትን ይመለከታል" ብሏል አቶ ጌታቸው።

በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን ህጻናት ከ7 ዓመት ህጻናት ጋር አንደኛ ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ስነ ልቦናዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው እንዚህን ህጻናት መርዳት የሚቻልበት ሁኔታን ያመቻቸ የትምህርት መርሃ ግበር መሆኑን ከአቶ ጌታቸው መግለጫ መረዳት ይቻላል።

በዚሁ መርሃ ግብር መሰረት ህጻናቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ክፍል ይደርሳሉ፤ በሚቀጥለው ሁለተኛ ዓመት በቀጥታ ወደ አራተኛ ክፍል እንዲሻገሩ የሚያስችል የትምህርት መርሃ ግብር ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የተቀላጠፈ የትምህርት መርሃ ግብር ከሃገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ ጋር እንዳይቃረን ተማሪዎችን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በመስጠት ማረጋገጥ መቻሉን አቶ ጌታቸው ተስፋይ ይናገራሉ። በዚሁም መሰረት 85 ከመቶ የተማሪዎቹ ቁጥር 80 ከመቶ ኣማካይ ውጤት በማስመዝገባቸው ምክንያት በመንግስት በኩል ተቀባይነት ማግኘት መቻሉን ሃላፊው ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት መርሃ ግብሩ በአምስት የትግራይ ክልል ወረዳዎች የሚገኙ ህጻናት ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል።

የአመሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ገብሩ ወደ ሕንጣሎ ወጀራት በመሄድ አፍ ጐል በተባለው ትምህርት ቤት ውስጥ በመሰጠት ላይ ያለውን የትምህርት መርሃ ግብር ጐብኝቷል።

ትግራይ ክልል ውስጥ ከ“Operation Rescue Ethiopia” በተጨማሪ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነ እየሱስ፣ የትግራይ ልማት ማሕበርና Wide Horizon የተባሉት ድርጅቶችም በ(ALFA) የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ መርሃ ግብር ውስጥ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙም አቶ ጌታቸው አክለው ገልጸዋል።

የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG