በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ የኮቺኔል ትል (የበለስ መዥገር)የሚያጠፋ መድሐኒት ቀመሙ

Security forces run from the site of a suicide attack after the second bombing in Kabul, Afghanistan. A double suicide bombing in central Kabul killed at least 26 people, including nine journalists. At least 50 people were wounded.

የኮቺኔል ትል የሚራባው በበለስ ተክል እንደመሆኑ መጠን በለስ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰውና እንስሳት ምግብነት ስለሚውል ትሉ ተክሉን በአጭር ዓመታት ውስጥ አውድሞታል።

በ2003 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል የገባው ትል ከፍተኛ ጥቅም ይገኝበታል በሚል ታቅዶ እንዲገባ መደረጉ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ሲሳይ ወልደገብርኤል ይገልፃሉ።

ዶክተር ሲሳይ ወልደገብርኤል
ዶክተር ሲሳይ ወልደገብርኤል

የኮቺኔል ትል የሚራባው በበለስ ተክል እንደመሆኑ መጠን በለስ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰውና እንስሳት ምግብነት ስለሚውል ትሉ ተክሉን በአጭር ዓመታት ውስጥ አውድሞታል።

የኮቺኔል ትል በንፋስና በበለስ ዝውውር በፍጥነት ስለሚዛመት ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በአብዛኛው በመቀሌና አከባቢው እንዲሁም በደቡባዊ የትግራይ ክልል በመዛመት ገበሬዎች ከበለስ ተክል ያገኙት የነበሩትን ጥቅም አሳጥቷቸዋል።

መንግስት የትሉን መዛመት ለመከላከል ከፍተኛ ባለሞያዎችን ከውጭ ሀገር በማምጣትም ጭምር ጥረት ብያደርግም አልተሳካለትም ብሏል ዶክተር ሲሳይ። ቀጥሎ የተካሄደው የመከላከል ዘመቻ ባህላዊ መንገድን የተከተለ እንደነበር አውስተው እሱም የታመመው የበለስ ተክል በመቁረጥና፣ በመቅበር እንዲሁም ገበያ ላይ የሚገኙትን መድሐኒቶችን በመጠቀም ለመከላከል እንደተመኮረ ያስረዳሉ። ቢሆንም ይኸም ውጤታማ ሊሆን አለመቻሉን ተናግረዋል።

ከዚህ ሁሉ ሙከራና ጥረት በኋላ ዶክተር ሲሳይ ከተፈጥሯዊ ተክሎች ቀምመው ትሉን ወይም መዥገሩን በቅፅበት ሊያጠፋ የሚችል መድሐኒት ቀምመው እንዳዘጋጁ ይፋ አድርገዋል። ዶክተር ሲሳይ፣ ይኽንን ምርምር ውጤታማ ለማድረግ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን አንድ ዓመት እንደወሰደባቸው ይናገራሉ።

መድሐኒቱ በገጠር አከባቢዎች ተመኩሮ ውጤታማ መሆኑን በተግባር ከተረጋገጠ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንደሰጣቸውም ገልጸዋል ዶክተር ሲሳይ።

ከአሁን በኋላ መድኅኒቱን በመጠቀም ተባዩን የመከላከል ኅላፊነት የመንግሥትና የባለድርሻ አካላት መሆኑን ዶክተር ሲሳይ አበክረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ የኮቺኔል ትል (የበለስ መዥገር) የሚያጠፋ መድሐኒት ቀመሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:30 0:00

XS
SM
MD
LG