ሐውዜን —
አርሶ አደር ኪዳኑ ግርማይ በምስራቁ የትግራይ ክልል በሐውዜን ወረዳ ከትግራይ የእርሻ ምርምር ተቋም ጋር ይሰራሉ። አየርላንድ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የእርሻ ተግባራዊ ምርምር ላይ ያተኮረ ስብሰባ በመሳተፍም ከማላዊና ሌሴቶ ከመጡት ገበሬዎች ጋራ የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸውን ገልጿል።
አቶ ኪዳኑ የተሻሻለ የእርሻ ዘዴ ተግበራዊ ለማድረግ የትግራይ የእርሻ ምርምር ተቋም ከአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያገኛቸውን የዘበናዊ የእርሻ ግብአቶችን ተጠቅመው ምርታማነትን በማሳደግ ኑሮዋቸውን የቀየሩ ብርቱ አርሶ አደር ናቸው።
አርሶ አደሩ በአዝርእት፣ ፍራፍሬና የንብ እርባታ በመሰማራት የቤተሰቦቻቸውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጣቸውም ይናገራሉ።
የትግራይ የእርሻ ምርምር ተቋም ከአየርላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ትግራይ ክልል ውስጥ በተመራማሪ ገበሬዎች አማካኝነት ተግባራዊ ምርምር ያካሂዳል።
ወደ አከባቢው የተጓዘው ግርማይ ገብሩ አርሶ አደሩን አነጋግሮ አንድ ልዩ ዝግጅት ልኳል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።