የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ጉዳይ በታንዛንያ እስር ቤት።
በሕገ ወጥ መንገድ የኬንያን ድምበር ተሻግራችሁዋል በመባል የተከሰሱ ከ28 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ኦሮሞ ስደተኞች ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የማርሳቢት ፍርድ ቤት መወሰኑ ታዉቋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ስደተኞቹ ጥገኝነት እንዲያገኙ ለኬንያ መንግስት ያቀረበዉ ጥያቄ አንድ ስደተኛ ከማስጠልል በስተቀር ተቀባይነት እንዳላገኘ ተናግሯል። እንዲመሰሱ የተደረጉት ስደተኞች ግን አሁን ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም።
ኢዮጵያውያኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በነበሩበት ጊዜ፣ ከረሃብና ከውኃ ጥም የተነሳ ሰዉነታቸዉ በጣም ተዳክሞ እንደነበረ የሃገሪቱ ፖሊስ አስታዉቀዋል። ባለሥልጣናት ለአሜርካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ ሌሎች ህገ-ወጥ የተባሉ ኢትዮጵያውያንም በኬይላ ታንዛንያ እስር ቤት ዉስጥ ይገኛሉ።
ሰሜን ኬንያ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉት ጥገኝነት ፈላጊ የኢትዮጵያ ዜጎች መብታቸው እንዲከበር ኬንያ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቅርንጫፍ ጠየቀ።
ባለፈዉ ሳምንት ፍጻሜ ኬንያ ቁጥራቸዉ 25 የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ ሰጠች ሲሉ በናይሮቢ የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወካይ ተናገሩ።
ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው በእግሊዝኛ ስሙ ምኅፃር (WTO) እየተባለ የሚታወቀው የዓለም የንግድ ድርጅት ጉባዔ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቀቀ። ድርጅቱ በዘንድሮው ስብሰባ የላይቤርያንና የአፍጋንስታንን የአባልነት ጥያቄ አጽድቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ በሚያሰሙ ኦሮሞዎች ላይ የሃይል እርምጃ እየወሰደ ነው ሲሉ በኬንያ የስደተኞች ማሕበረሰብ አባላት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ናይሮቢ ላይ የተቃውሞ ስብሰባ አካሄዱ።
ኢትዮጵያና ኬንያ በሁለቱ ሀገራት ድምበር ከተማ በሆነችዉ ሞያሌ ዉስጥ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ስምምነት ተፈራረሙ። በዚህ የስምምነት ፊርማ ስነ-ሥርዓት ላይም የሁለቱ ሀገራት መሪዎችና ምንስትሮች ተገኝተዋል።