በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረገጣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ አምነስቲ


ትላንት በኬንያ ናይሮቢ ድርጀቱ ባደረገዉ ስብሰባ ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላ በኢትዮጵያ ያለዉ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እስካሁን ቀጥሎ ለብዙ የኢትዮጵያ ዜጎች መታሰርና መሰደድ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ዉስጥ እየተፈጸመ ያለዉየሰብዓዊ መብት ረገጣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል ገለጸ።

ድርጅቱ ትላንት በናይሮቢ ኬንያ ባደረገዉ ስብሰባ ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላ በኢትዮጵያ ያለዉ የሰብዓዊ መብትረገጣ እስካሁን እንደቀጠለ ነው፡ ለብዙ የኢትዮጵያ ዜጎች መታሰርና መሰደድ ምክንያትሆኗል ብሏል። በዉይይቱ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ረገጣ የተፈጸመባቸዉሰዎች ቀርበዉ የምስክርነት ቃላቸዉን ሰጥተዋል።

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ባሉትየስደተኞች ሰፈር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ስደተኞችም በስብሰባዉ ተካፍለዋል። ስደተኞቹየተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) በአግባቡ መብታችንንእያስጠበቀልን አይደለም በማለት ቅሬታቸውን በስብሰባዉ ላይ ለተገኙለስደተኞች ድርጅቱ ተወካይ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረገጣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ አምነስቲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG