በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞያሌ በደረሰ የጎርፍ ማጥለቅለቅ ሶስት ሰዎች ሞቱ ንብረት ወደመ


በኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ የምትገኘው የሞያሌ ከተማ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/
በኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ የምትገኘው የሞያሌ ከተማ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/

ባለፈዉ እሁድ በሞያሌ ከተማ የጣለ ከባድ ዝናብ በሰዉ ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። ዝናቡን ተከትሎ በአካባቢዉ በደረሰ ከባድ ጎርፍ ማጥለቅለቅ የሶስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢዉ የቀይ መስቀል ባልደረባ ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል።

በሞያሌ ከተማ ከባድ ዝናብ ዘንቦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። ከቅዳሜ ምሽት እስከ እሁድ ድረስ የዘነበዉ ዝናብ የ 3 ሰዉ ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢዉ አርብቶ አደሮች ንብረት ላይም መጠነኛ ጉዳት አድርሷል።

የሞያሌ ካርታ
የሞያሌ ካርታ

ዝናቡን ተከትሎ ከተማዋን ያጥለቀለቀዉ ጎርፍ በኢትዮ-ኬንያ ድምበር ላይ ያለዉን ድልድይ በማፈራረሱ እስከ ትናንት ጠዋት ድረስ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ክፍት አለመሆኑን የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል። በከተማዋ ዙርያ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችም ጎርፉ ላሞቻቸዉንና ፍየሎቻቸዉን እንደወሰደባቸዉ ይናገራሉ። አቶ ለበን ጎልቻ የሞያሌ አካባቢ ነዋሪ ናቸዉ፣ እሳቸዉ እንደሚሉት በኬንያ ሞያሌ በኩል ዝናቡ በአርብቶ አደሮች ላይ ጉዳት ማድረሱን ነዉ።

"ከባድ ዝናብ ነዉ የዘነበዉ፣ቅዳሜ ምሽት 9፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ እስከ እሁድ ቀነ_6፡00 ሰዓት ነዉ የዘነበዉ። አሁንም መንገዶች ተዘጋግተዋል፣ ከቦር፣ ከዳቤል፣ ወደ የኬንያ ሞያሌ የሚወስዱ መንገዶች ከአገልግሎት ዉጪ ሆነዋል፣ በተጨማሪም የኬንያን ሞያሌንና የኢትዮጵያን ሞያሌ የሚያገናኘዉ መንገድም ድልድይዉ በሞላ ወንዝ በመወሰዱ አሁን ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ዝናቡ ብዙ ነገር ነዉ ያጠፋዉ፣ ወደ 25 የሚሆኑ ፍየሎች ና 4 ከብቶች በጎርፍ ተወስደዋል፣ ቤቶችንንም አወድመዋል።" ብለዋል።

በኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ የምትገኘው የሞያሌ ከተማ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/
በኢትዮ - ኬንያ ድምበር ከተማ የምትገኘው የሞያሌ ከተማ እ. አ. አ. 2008 /ፋይል ፎቶ/

ዝናቡ በተለይ ከሞያሌ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚትገኘዉን ሜጋ የተባለችአነስተኛ መንደር መጠነኛ ጉዳት አድርሶባታል።

አርብቶ አደር ደደቻ ወራብ የሜጋ ነዋሪ ናቸዉ፣ በተለይ ከሜጋ ወደ ሞያሌ የሚወስደዉን መንገድ ለመሥራት ተገድቦ የነበረዉ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በንብረታችን ላይ ጉዳት አድርሰዋል ይላሉ። "ከሜጋ ሞያሌ የሚወስደዉን መንገድ እየሰራ ያለዉ የህንዱ GMC ካምፓኒ የአካባቢዉን ወንዝ ይፈስበት የነበረዉን መንገድ በመዝጋቱ ወንዙ ወደ ኋላ ወደ እኛ ተመለሰ። በዚህ ምክንያትም ወደ 250 ቤቶች በተከሰተዉ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተወስደዉብናል።" ብለዋል።

በጣለዉ ከባድ ዝናብና በተከተለዉ ጎርፍ ሕይወታቸዉ ያለፈዉ 3 ሰዎች የኢትዮጵያ ዜጎችመ ሆናቸዉን ከኬንያ ቀይመስቀል የተገኘ መረጃ ይጠቁማል። በጎርፉ ሳብያም የዉሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይነሱ ቀይ መስቀል ነዋርዎቹን እያስጠነቀቀ መሆኑ ተገልጿል። ከወራት በፊት በሞያሌ አካባቢ በተቀሰቀሰዉ የኮሌራ በሽታ ሁለት ሰዎች መሞታቸዉ የሚታወስ ነዉ

ሜጋ በምትባል አነስተኛ መንደር አካባቢ ድልድይ እንዲሰራለት ተገድቦ የነበረ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሶ፣ ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ ከናይሮቢ አድርሶናል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

በሞያሌ በደረሰ የጎርፍ ማጥለቅለቅ ሶስት ሰዎች ሞቱ ንብረት ወደመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG