በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህገ - ወጥ መንገድ ናይሮቢ ገቡ የተባሉ 23 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል


በህገ - ወጥ መንገድ ናይሮቢ ገቡ የተባሉ 23 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል
በህገ - ወጥ መንገድ ናይሮቢ ገቡ የተባሉ 23 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል

በህገ - ወጥ መንገድ ናይሮቢ ገቡ የተባሉ 23 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ሰሜን ናይሮቢ ካሃዋ ዌስት በሚባል ቦታ ነው። ትላንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል። ጉዳያቸዉን የተመለከተዉ የክያምቡ ግዛት ፍርድ ቤት በቂ ማስረጃና ምርመራ እስኪደረግ፥ የሳምንት ቀጠሮ ሰጥተዋቸዋል።

ቁጥራቸዉ 23 የሚሆን በህገ - ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያዉያን በትላንትናዉ ዕለት ከናይሮቢ በስተ - ሰሜን ካሃዋ ዌስት በሚባል ቦታ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ኬንያ የገቡት በቅርቡ እንደሆነና ያመጣቸዉም ግለሰብ ሥራ ለማስቀጠር መሆኑን ለፖሊስ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ያስጠለላቸዉ ግለሰብ ማንነት ለጊዜዉ ያልታወቀ ሲሆን የአካባቢዉ ነዋርዎች ግን በዚሁ ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ተገደለ በተባለዉ የሞተር ቢሲክሌት አሽከርካሪ ግድያ የኢትዮጵያዉያኑ እጅ አለበት በማለት የጥቃት እርምጃ ሊያደርሱባቸዉ ነበር። በዚህ ምክንያትም ነዋሪዎቹ በአካባቢዉ ከነበረዉ የፖሊስ ኃይል ጋር የተጋጩ ሲሆን የኬንያ ፖሊስም በጊዜዉ ሁኔታዉን ለመቆጣጠር የማስጠንቀቅያ ተኩስ ተኩሷል።

ኢትዮጵያዉኑ በናይሮቢ ካሃዋ ዌስት ከተያዙ ቦኋላም ወደ ኪያሙምቢ ፖሊስ ጣብያ የተወሰዱ ሲሆን ወድያዉም በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብታችሁዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ትላንት ከሰዓት በኋላም በኪያምቡ ግዛት ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ማንነታቸዉን የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ስለሌና የኬንያ ኢሚግሬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ተወካይም ባለመገኘታቸዉ ችሎቱ ለሚመጣዉ ረቡዕ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያዉያኑ ሞተ በተባለዉ ግለሰብ ግድያ ዉሥጥ እጃቸዉ አለበት ወይ ብለን የኪያምቡ ግዛት ፖሊስ ምክትል ኃላፊ የኑሆኑትን ኦፍሰር ጆንሥተን ሊያምቢላን ጠይቀን ነበር። ”እንግዴ ያ ምርመራ እየተካሄደበት ያለ ጉዳይ ነዉ። ነገር ግን እነሱ እጃቸዉ በእዚህ ወንጀል ዉስጥ የለበትም። እነሱ እንደተሳተፉበት የሚያሳይ ምንም ዓይነት መረጃ የለም” ብለዋል።

እንደ ኦፊሰር ሊያምባላ ኢትዮጵያዉያኑ በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ከ 23ቱ ኢትዮጵያዉያን አንደኛው ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ወይም ፓስፖርት በማሳየቱ በነጻ ሲፈታ ሌሎቹ 22 ግን መታወቅያ ስለሌላቸዉ ወደ ኬንያ የገባችሁት በህገ - ወጥ መንገድ ነው የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። በጉዳዩም ላይ ብይን ለመስጠት ችሎቱ የሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል። የኬንያ ኢሚግሬሽን ጉዳይ ቢሮ በመጪዉ ረቡዕ ሙሉ ሪፖርት ይዞ እንዲቀርብ፣ የኢትዮጵያዉኑም ማንነት በጥልቅ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የኬንያ ፖሊስ ሰሞኑን የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ካስተላለፈ በኋላ በተለይ በዋና ዋና የሃገሪቱ ከተሞች ዉስጥ አሰሳ በማካሄድ ላይ ሲሆን በትላንትናዉ ዕለት ብቻ ከ 23ቱ ኢትዮጵያዉያን ዉጪ፥ ሌሎች 119 የሚሆኑ የናይጄርያና የኢትዮጵያ ዜጎች ናይሮቢ ዉስጥ ስታረሄ በሚባል ቦታ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዉለዋል።

የስታሬሄ አካባቢ ፖሊስ ጣብያ ኦፊሰር አሊስ ኪሜሊ ስታንዳርድ (The Standard) ለተባለ የኬንያ ጋዜጣ ሲናገሩ፥ በህገ - ወጥ መንገድ ወደ ናይሮቢ የገቡት እኚህ የናይጄርያና የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች፥ ከአካባቢዉ ኃላፊዎች የመታወቂያ ካርድ ለመዉሰድ ሲሞክሩ ተይዘዋል ብለዋል።

ሃላፊዋ ውይም ኦፊሰሯ በማከልም አንዳንዶቹ በወንጀል ስራ ላይ ሲሳተፉም ይስተዋላል ሲሉ አስረድተዋል።

ካሃዋ ዌስት የተያዙት ኢትዮጵያዉን በመጪዉ ዓርብ ፍርድ ቤት እስኪቀርቡ ድረስ፥ በናይሮቢ ኢንዱስትርያል ኤርያ በሚባል ቦታ በሚገኘዉ ሪማንድ የእስረኞች ማቆያ ዉስጥ ይቆያሉ።

ለአሜርካ ድምጽ ገልሞ ዳዊት ከናይሮቢ የላከውን ዘገባ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

በህገ - ወጥ መንገድ ናይሮቢ ገቡ የተባሉ 23 ኢትዮጵያዉያን በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG