በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የድምበር ከተማ ሞያሌ ነዋሪዎች ሰሞኑን በኮሌራ በሽታ እየተቸገሩ መሆናቸዉን ይገልጻሉ

ፋይል ፎቶ - የኮሌራ በሽታ በንጽሕና ጉድለት የሚተላለፍ በሽታ ነው
ፋይል ፎቶ - የኮሌራ በሽታ በንጽሕና ጉድለት የሚተላለፍ በሽታ ነው

ነዋሪዎቹ ይህ ችግር ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ አንድ አዛዉንት እና አንድ ህጻን ሕይወታቸዉ ሲያልፍ አንዲት ዕርጉዝ ሴት የጸነሰችዉ ጽንሥ በዚሁ በያዛት በሽታ መጨንገፉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የድምበር ከተማ ሞያሌ ነዋሪዎች ሰሞኑን ኮሌራ በሽታ እየተቸገሩ መሆናቸዉን ለአሜርካ ድምጽ ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ይህ ችግር ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ አንድ አዛዉንት እና አንድ ህጻን ሕይወታቸዉ ሲያልፍ አንዲት ዕርጉዝ ሴት የጸነሰችዉ ጽንሥ በዚሁ በያዛት በሽታ መጨንገፉን ተናግረዋል።

የሞያሌ ከተማ ጤና ጣብያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቦሩ ሁቃ ችግሩ መከሰቱን አምነው፣ ነገር ግን የሰዉ ህይወት አልፏል የተባለዉን አስተባብለዋል።

ችግሩ ጋምቦ በመባል በምታወቅ ቦታ ወደ ሞያሌ ከተማ መጣ ያሉት አቶ ቦሩ፣ በተለይ በሞያሌ ከተማ በ01 እና በ02 ቀበሌዎች ችግሩ በሥፋት ታይቶ እንደነበረ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም ነገሩን በቁጥጥር ሥር ዉሏል ሲሉ፣ ነዋሪዎች ግን አሁንም ይህ በሽታ ሰዎችን በማስቸገር ላይ ነዉ በማለት ይናገራሉ። ገልሞ ዳዊት ያጠናቀረው ዘገባ አለ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ የድምበር ከተማ ሞያሌ ነዋሪዎች ሰሞኑን በኮሌራ በሽታ እየተቸገሩ መሆናቸዉን ይገልጻሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:18 0:00

XS
SM
MD
LG